- Sputnik አፍሪካ, 1920
Sovereignty Sources
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

የአሜሪካ የጋዛ ዕቅድ፡ በረከት ወይስ ስውር ዓለማ ?

የአሜሪካ የጋዛ ዕቅድ፡ በረከት ወይስ ስውር ዓለማ?
ሰብስክራይብ

''ከጊዜ ወደ ጊዜ አሜሪካ ኃይሏ እየተሸረሸረ መምጣቱን በማሰብ 'አሜሪካ ድጋሚ ትልቅ እናደርጋለን' የሚል መርህ በመያዝ ነው ይሄንን አቋም እያሳዩ ያሉት - የዓለም አቀፍ አሰላለፍም ይሁን ይዘን የመጣናቸው ፖሊቲካዊም ይሁን ኢኮኖሚያዊ እሳቤዎች የአንድ ወገን ናቸው፣ ወደ አንድ ወገን ያጋደሉ ናቸው[....] '' ሲሉ በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ አበራ ሄቢሶ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ሁለት ጉዳዮችን በሚዳስሰው ፕሮግራማችን በመጀመሪያው ክፍል አሜሪካ በጋዛ ለመተግበር የነደፈችውን ዕቅድ፣ የፍልስጤማዊውያን ሉዓላዊነት፣ የራሷን ጥቅም የማስጠበቅ አካሄዷን እና ተያያዥ ጉዳዮችን በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ አበራ ሄቢሶ ጋር ቃኝተናቸዋል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ኢትዮጵያ ለሩሲያ ቁልፍ የአፍሪካ አህጉር አጋር እንደመሆኗ ከቴክኖሎጂ ትብብር ፍላጎት ጋር በማዛመድ የሶፍትዌር፣ ሳይበር ሴኪዩሪቲ እና የሠው ሠራሽ አስተውሎት አበልጻጊው አቤል በነበሩ እና በወሎ ዩኒቨርሲቲ የሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ መምህርት ቤዛዊት እንድሪስ ጋር ተወያይተናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0