የኮትዲቯር ፕሬዚዳንት አላሳን ዋታራ ለአራተኛ ጊዜ ቃለ መሃላ ፈጸሙ
20:19 08.12.2025 (የተሻሻለ: 20:24 08.12.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኮትዲቯር ፕሬዚዳንት አላሳን ዋታራ ለአራተኛ ጊዜ ቃለ መሃላ ፈጸሙ
90 በመቶ ድምፅ በማግኘት በድጋሚ የተመረጡት የኮትዲቯር ፕሬዚዳንት፤ በአቢጃን በሚገኘው ፕሬዚዳንታዊ ቤተ-መንግሥት ውስጥ በሕገ-መንግሥታዊ ዳኞች ፊት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
ዋታራ ቀኝ እጃቸውን በማንሳት እና ግራ እጃቸውን በሕገ-መንግስቱ ላይ አሳርፈው፤ "ሕገ-መንግሥቱን አከብራለሁ፣ በታማኝነት እከላከላለሁ፣ ብሔራዊ አንድነትን እወክላለሁ" በማለት ቃል ገብተዋል።
"ታላቁን የብሔራዊ ኒሻን" የተቀበሉት ዋታራ፤ "የሀገርን የበላይ ጥቅም ለማስጠበቅ የሥራ ግዴታዬን በትጋት እወጣለሁ" ሲሉም ቃለ መሃላ ሰጥተዋል።
ከአፍሪካ መሪዎች መካከል የአንጎላ፣ ኮንጎ፣ ጅቡቲ፣ ጋቦን፣ ሴኔጋል፣ ኮሞሮስ፣ ጋና፣ ጋምቢያ፣ ላይቤሪያ፣ ሴራሊዮን እና ሞሪታኒያ ርዕሰ ብሔራትን ጨምሮ በርካቶች በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X