- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

የግብርና መድህን ሽፋን በኢትዮጵያ

የግብርና መድህን ሽፋን በኢትዮጵያ
ሰብስክራይብ
“የግብርና መድህን በአገራችን ውስጥ የሚፈለገውን ያህል አላደገም፡፡ ከአጠቃላይ ኢንዱስትሪው ከሚሰጠው የመድህን ሽፋን የግብርና ኢንሹራንስ ስናየው ከ 1 በመቶ አይዘልም፡፡ እስካሁን የተሰራው፡፡ እሱም ቢሆን ደግሞ በአብዛኛው ኮሜርሻል ፋርም ጋር የሚያያዝ ነው፡፡” ሲሉ የኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ባለሙያዎች ማህበር ምክትል ፕሬዝደንት እንዲሁም የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማኅበር የስትራቴጂ እና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍቅሩ ፀጋዬ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል በኢትዮጵያ ውስጥ የግብርና መድህን ያለበትን ደረጃ እና አገልግሎቱን ተደራሽ በማድረግ ረገድ እያጋጠሙ ስላሉ የተለያዩ ተግዳሮቶች የኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ባለሙያዎች ማህበር ም/ፕሬዝደንት እንዲሁም የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማኅበር የስትራቴጂ እና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍቅሩ ፀጋዬ ጋር የተወያየን ሲሆን፤ የሁለተኛውን የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ክላስተር ፕሮጀክት በይፋ የማስጀመር መርሀ-ግብር አስመልክቶ ያዘጋጀነው መሰናዶም ተካትቷል፡፡

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0