- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

የአፍሪካ አህጉራዊ የካሳ ጥያቄ ፡ የቅኝ ግዛት ዘመኑን በደል ምን ሊክሰው ይችላል ?

የአፍሪካ አህጉራዊ የካሳ ጥያቄ ፡ የቅኝ ግዛት ዘመኑን በደል ምን ሊክሰው ይችላል ?
ሰብስክራይብ
“ገንዘብ እጅግ ጥሩ ያልሆነ የካሳ ዓይነት ይመስለኛል። የአውሮፓ አፍሪካን የመቆጣጠር ጥቅም፣ ከቅኝ ግዛት፣ ከአዲሱ ቅኝ ግዛት እና ከባርነት የተገኘው፣ ዘላቂ ችግር ነው። ስለዚህ፣ የካሳው ጥቅምም እንዲሁ ዘላቂ መሆን አለበት ብዬ አስባለሁ።[…]የቀድሞ ጨቋኞች በአህጉሪቱ ላይ የአንድነት መሠረተ ልማቶችን መገንባት አለባቸው። ይህ ማለት እንደ ካሳ ፣ መላውን አፍሪካ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ አፍሪካ የሚያገናኝ የባቡር ሐዲድ መገንባት አለበት።[...] ይህ አፍሪካ ዛሬ ከምናደርገው በበለጠ መልኩ በውስጥዋ ውጤታማ ንግድ እንድትፈጽም ያስችላታል።” ሲሉ የፓን-አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ እና አማካሪ ካባላ ጆን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ፣ በመጀመሪያው ክፍል የፓን-አፍሪካኒዝም አቀንቃኝና አማካሪ ካባላ ጆን ጋር በመሆን የአፍሪካን አህጉራዊ የካሳ ጥያቄ ፖለቲካዊ፣ ሞራላዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተገቢነት ተወያይተናል ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የዲጂታል ፋይናንስ ለውጥ እና እድገት እንዲሁም አሳታፊነት የኢትዮ-ኢንክሉሲቭ ፋይናንስ ቴክኖሎጂ አ.ማ. ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከሆኑት ከአቶ አዋሽ ባቴ፣ እና የአሪፍፔይ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረድኤት ጽጌብርሃን ጋር ያደረገነው ቆይታ በሁለተኛው ክፍል ተዳስሷል፡፡

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox

አዳዲስ ዜናዎች
0