በኢትዮጵያ ባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የቱሪዝም ፍሰት በመጨመሩ የአካባቢው ገቢ እድገት አሳይቷል ተባለ
19:27 07.12.2025 (የተሻሻለ: 20:14 07.12.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ ባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የቱሪዝም ፍሰት በመጨመሩ የአካባቢው ገቢ እድገት አሳይቷል ተባለ
በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ እና በተሻሻለ መሠረተ ልማት ምክንያት የብሔራዊ ፓርኩ ጎብኚዎች ቁጥር ባለፈው ሩብ ዓመት ከ17 በመቶ በላይ ጭማሪ አሳይቷል ሲል የፓርኩ አስተዳደር አስታውቋል። ከጠቅላላ ጎብኚዎች መካከል ግማሽ ያህሉ የውጭ ቱሪስቶች መሆናቸውን አያይዞ ገልጿል፡፡
የፓርኩ ሥራ አስኪያጅ ሻሚል ከድር ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፤ ይህ ዕድገት የፓርኩም ሆነ የአካባቢው ማህበረሰብ ገቢ ከፍ እንዲል በማድረግ፤ የአካባቢው ቱሪዝም ማህበራት የሩብ ዓመት ገቢ ወደ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር እንዲያድግ አድርጓል፡፡
ዕድገቱ በዩኔስኮ ዝርዝር ውስጥ በመካተቱ፣ በተሻሻለ የማስተዋወቅ ሥራ እንዲሁም በዋና ዋና የመንገድ እና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች የመጣ እንደሆነ ኃላፊዎች ጠቁመዋል፡፡
በማደግ ላይ ያለው ዘርፍ እንደ በቅሎ ኪራይ እና ዕቃ የማመላለስ አገልግሎቶች የኑሮ ምንጭ ሆኖ እያገለገለ ነው ተብሏል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች ከቱሪዝም በቀጥታ ተጠቃሚ መሆናቸው በማህበረሰብ መር ቁርጠኝነት የፓርኩ ጥበቃ እንዲጠናከር አድርጓል ሲሉ የፓርኩ ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/9
© telegram sputnik_ethiopia

2/9
© telegram sputnik_ethiopia

3/9
© telegram sputnik_ethiopia

4/9
© telegram sputnik_ethiopia

5/9
© telegram sputnik_ethiopia

6/9
© telegram sputnik_ethiopia

7/9
© telegram sputnik_ethiopia

8/9
© telegram sputnik_ethiopia

9/9
© telegram sputnik_ethiopia
1/9
© telegram sputnik_ethiopia
2/9
© telegram sputnik_ethiopia
3/9
© telegram sputnik_ethiopia
4/9
© telegram sputnik_ethiopia
5/9
© telegram sputnik_ethiopia
6/9
© telegram sputnik_ethiopia
7/9
© telegram sputnik_ethiopia
8/9
© telegram sputnik_ethiopia
9/9
© telegram sputnik_ethiopia