“በሞናኮ ከሚገኙት ውድ መኪናዎች መካከል ግማሹ የዩክሬን ታርጋ አላቸው”፤ የሀብቱ ምንጭ ከየት ነው? - ትራምፕ ጁኒየር
19:00 07.12.2025 (የተሻሻለ: 19:04 07.12.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
“በሞናኮ ከሚገኙት ውድ መኪናዎች መካከል ግማሹ የዩክሬን ታርጋ አላቸው”፤ የሀብቱ ምንጭ ከየት ነው? - ትራምፕ ጁኒየር
“በዚህ ክረምት በሞናኮ ነበርኩ...በመደበኛ ቀን 50 በመቶ የሚሆኑት ቡጋቲዎች፣ ፌራሪዎች እና የመሳሰሉ ወድ መኪናዎች ሁሉም የዩክሬን ታርጋ ነበራቸው” ሲሉ የዶናልድ ትራምፕ ልጅ በ2025 ዶሃ ፎረም ላይ ተናግረዋል።
ዩክሬን “ሀብታም አይደለችም” ያሉት አሜሪካዊው የንግድ ሰው፤ የእንደዚህ አይነት ቅንጦት ሕጋዊነት ላይ ጥያቄ አንስተዋል።
“በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር” በማባከን ተከሰው የታሠሩ የቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ጨምሮ በዩክሬን ባለሥልጣናት ላይ የወጡትን የቅርብ ጊዜ የሙስና ክሶች ጠቅሰዋል።
አስተያየቱ አንድሬ ይርማክን ጨምሮ በዩክሬን የቀድሞ ባለሥልጣናት እና የዘለንስኪ አጋር ቲሙር ሚንዲችን ያካተተ ሰፊ የኃይል ዘርፍ ሙስና ቅሌት መሰማቱን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡ በተካሄዱ ድንገተኛ ምርመራዎች በውጭ ገንዘብ የተሞሉ ቦርሳዎች የተገኙ ሲሆን ከፍተኛ ተጠርጣሪዎች ከሀገሪቱ ሸሽተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X