በአዲስ አበባ በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የተደገፈ የተቀናጀ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት አሰጣጥ በይፋ ተጀመረ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበአዲስ አበባ በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የተደገፈ የተቀናጀ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት አሰጣጥ በይፋ ተጀመረ
በአዲስ አበባ በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የተደገፈ የተቀናጀ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት አሰጣጥ በይፋ ተጀመረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.12.2025
ሰብስክራይብ

በአዲስ አበባ በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የተደገፈ የተቀናጀ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት አሰጣጥ በይፋ ተጀመረ

ዲጂታል ስርዓቱ ከመጪው ሕዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በ50 ወረዳዎች ተግባራዊ መደረግ እንደሚጀምር የከተማዋ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

አዲሱ አሠራር በአገልግሎት አሰጣጥ ፍትሐዊነትን እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ቁልፍ መፍትሄ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡

"ይህ አዲስ የተቀናጀ ዲጂታል ሥርዓት አዲስ አበባ ባለፉት 14 ዓመታት ስትጠቀምባቸው የነበሩ በወረቀት ይሰጡ የነበሩ አገልግልቶችን ይተካል፡፡ ነዋሪዎች የሲቪል ምዝገባን እና ሌሎች አገልግሎቶችን በአካል መምጣት ሳይጠበቅባቸው ባሉበት እንዲያገኙ የሚያስችል ሆኖ የተሠራ ነው" ብለዋል፡፡

ቴክኖሎጂው ከተቋሙ የሚመነጩ መረጃዎችን በመሰነድ ትክክለኛ ፖሊሲ ለመቅረጽና እቅድ ለማዘጋጀት ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን የሚያስተሳስረው ይህ የዲጂታል አሠራር በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የለማ መሆኑን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0