"ሼክስፒርን ከትምህርት ስርዓታችን እናውጣ"፤ ለአፍሪካውያን የአፍሪካ ሥነ-ጽሁፍ ያሻል - ናይጄሪያዊ ደራሲ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ"ሼክስፒርን ከትምህርት ስርዓታችን እናውጣ"፤ ለአፍሪካውያን የአፍሪካ ሥነ-ጽሁፍ ያሻል - ናይጄሪያዊ ደራሲ
ሼክስፒርን ከትምህርት ስርዓታችን እናውጣ፤ ለአፍሪካውያን የአፍሪካ ሥነ-ጽሁፍ ያሻል - ናይጄሪያዊ ደራሲ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.12.2025
ሰብስክራይብ

"ሼክስፒርን ከትምህርት ስርዓታችን እናውጣ"፤ ለአፍሪካውያን የአፍሪካ ሥነ-ጽሁፍ ያሻል - ናይጄሪያዊ ደራሲ

መደበኛ የምዕራባውያን ጽሑፎችን በአፍሪካውያን ደራሲያን ሥራዎች መተካት የቅኝ ግዛት አስተሳሰብን ለማስወገድ እና ትክክለኛ የአፍሪካ ትርክቶች ላይ የተመሠረተ የትሪሊዮን ዶላር የፈጠራ ኢኮኖሚ ለመገንባት አስፈላጊ ነው ሲሉ አዬ-ኮ-ኦቶ በመባል የሚታወቁት ካሽ ኦናዴሌ ለናይጄሪያው ፓንች ጋዜጣ ተናግረዋል።

ዋና ፍልስፍናው፦ ለአፍሪካ ልማት የአፍሪካ ትርክቶች

የኦናዴሌ ተልዕኮ ሥነ-ጽሑፍ መነሻ ባሕሉን ማገልገል አለበት በሚለው እምነት የተመራ ነው። ናይጄሪያዊ-አሜሪካዊው ደራሲ ጽሁፋቸውን በአሜሪካ ወይም በአውሮፓ አውድ መቃኘታቸው መጨረሻው "አሜሪካን ማሻሻል" እና የውጭ አሳታሚዎችን ብቻ እንደሚጠቅም የደረሱብትን የግል ግንዛቤ አስታውሰዋል።

“ይህ ሀገሬን እንዴት ያሻሽላል?” ሲሉ ደራሲው፣ ገጣሚውና ፈላስፋው ጠይቀዋል።

ከ100 በላይ የፈጠራ ሥራዎችን ያሳተሙት ደራሲው፤ አሁን ሥራቸውን ናይጄሪያ ውስጥ በማዘጋጀት ኢኮኖሚያዊ እና ባሕላዊ ጥቅሙ ሀገር ውስጥ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

የመጨረሻ ግባቸው የአፍሪካ ወጣቶች የራሳቸውን እውነታ በሥነ-ጽሑፍ ውስጥ እንዲመለከቱ በማድረግ ራሱን የቻለ የፈጠራ ሥነ-ምህዳር መፍጠር ነው።

የሼክስፒር ትችት እና የትምህርት ስርዓት ማሻሻያ

"ዊልያም ሼክስፒርን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሥርዓተ ትምህርታችን ውስጥ ማሰራጨታችንን እስከቀጠልን ድረስ ልጆቻችን ከቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ሊላቀቁ አይችሉም።"

ኦናዴሌ፤ ከሀገር ውስጥ ደራሲዎች ለሼክስፒር ቅድሚያ መስጠት በተዘዋዋሪ ለተማሪዎች የውጭ ታሪኮች እና መቼቶች የተሻሉ መሆናቸውን ይነግራል ብለዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0