ኢትዮጵያ በምርት ዘመኑ 1.2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በበጋ ስንዴ መሸፈኗ ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በምርት ዘመኑ 1
ኢትዮጵያ በምርት ዘመኑ 1 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.12.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በምርት ዘመኑ 1.2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በበጋ ስንዴ መሸፈኗ ተገለፀ

ሀገሪቱ ከ4.2 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በማልማት ወደ 175 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለማምረት በያዘችው እቅድ፤ እስካሁን ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሄክታር መሬት መታረሱን የግብርና ሚኒስቴር የሰብል ልማት ዋና ሥራ አስፈፃሚ እያሱ ለማ ተናግረዋል።

እንደ ኃላፊው ገለፃ፦

ከ531,564 ሄክታር በላይ የሚሆነው መሬት በግሉ ዘርፍ የሚለማ ነው፡፡

179,934 ሄክታር መሬት ላይ ከ3.8 ኩንታል በላይ ምርት ተገኝቷል።

የግብርና ሚኒስቴር ከክልል ኃላፊዎች ጋር በመተባበር የተቀመጠውን ከፍተኛ የምርት ግብ ለማሳካት እየሠራ መሆኑን ለሀገር ውስጥ ሚዲያ አስታውቀዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0