ቡሩንዲ የኤም23 አማፂያንን ድንበር ተሻግረው የቦምብ ጥቃት ፈፅመዋል ስትል ከሰሰች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱቡሩንዲ የኤም23 አማፂያንን ድንበር ተሻግረው የቦምብ ጥቃት ፈፅመዋል ስትል ከሰሰች
ቡሩንዲ የኤም23 አማፂያንን ድንበር ተሻግረው የቦምብ ጥቃት ፈፅመዋል ስትል ከሰሰች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.12.2025
ሰብስክራይብ

ቡሩንዲ የኤም23 አማፂያንን ድንበር ተሻግረው የቦምብ ጥቃት ፈፅመዋል ስትል  ከሰሰች

የአካባቢው ሚዲያዎች የቡሩንዲ ባለሥልጣናትን ጠቅሰው እንደዘገቡት፣ ቦንቦቹ በኮንጎ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ሰሜናዊ ምዕራብ ከተማ ቺቢቶኬ ውስጥ አርፈዋል።

የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤድዋርድ ቢዚማና በሰጡት መግለጫ፣ “እንዲህ ዓይነቱ ጠብ አጫሪነት ተቀባይነት የለውም፤ የቡሩንዲን ሕዝብን ለመጠበቅ ተገቢው እርምጃ ይወሰዳል” ብለዋል።

የአማፂ ቡድኑ የጥቃቱን ኃላፊነት አልወስድም ሲል በፍጥነት አስተባብሏል፤ በምትኩ የቡሩንዲ እና የኮንጎ የመንግሥት ኃይሎች በሰሜንና ደቡብ ኪቩ በሕዝብ በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ላይ የተቀናጀ የአየር እና የመድፍ ጥቃት መፈጸማቸውን እና በዚህም ምክንያት 23 ንፁሃን ዜጎች እንደተገደሉ ተናግሯል።

ይህ የክስ ልውውጥ የደቡብ ኪቩ ውጊያው ከጠነከረ ወዲህ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ የተሰማ እጅግ በጣም ጉልህ የሆነ የድንበር ጥሰት እንደሆነ ተዘግቧል።

ጥቃቱ የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ በምስራቃዊ ኮንጎ የከረመውን ግጭት ለመፍታት በዋሽንግተን ዲሲ በአሜሪካ አስተናጋጅነት በተካሄደው የሰላም ንግግር ላይ ከተሳተፉ ከጥቂት ቀናት በኋላ የተፈጸመ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0