በሱዳን ዳርፉር የዓለም የምግብ ፕሮግራም የእርዳታ መኪና ጥቃት ተፈፀሞበት ሾፌሩ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል

በሱዳን ዳርፉር የዓለም የምግብ ፕሮግራም የእርዳታ መኪና ጥቃት ተፈፀሞበት ሾፌሩ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል
የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም እንዳስታወቀው፣ ይህ አደጋ የተከሰተው በአማፂያን ኃይሎች ቁጥጥር ሥር በሚገኘው ሰሜን ዳርፉር ክልል ውስጥ ካለው ከሐምራ ኤል-ሼክ አቅራቢያ ነው። 39 የእርዳታ መኪኖችን ያቀፈው ይህ የተሽከርካሪዎች ስምሪት (ኮንቮይ) በረሃብ ለተጎዳችው ታዊላህ ከተማ ከ700 ሺህ ለሚበልጡ ተፈናቃዮች ዕርዳታ ለማድረስ ሲሞክር ነበር።
ኢላማ የሆነው የጭነት መኪና በሜካኒካዊ ጥገና ምክንያት ከዋናው ኮንቮይ ተነጥሎ በሄደበት ወቅት ጥቃቱ የተፈጸመበት ሲሆን፣ የመኪናው የፊት ክፍል ወድሟል። ሹፌሩም አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ እንዲያገኝ ተደርጓል ሲል ድርጅቱ አስታውቋል።
የጭነት መኪናዎች ኮንቮይ፣ ታዊላህ ለመድረስ በወር ወደ 100 የሚጠጉ የእርዳታ መኪናዎች በሚጠቀሙበት ወሳኝ የ1 ሺህ ኪሎ ሜትር የአቅርቦት መስመር ላይ ይጓዝ ነበር። በአማፂያኑ የሰዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ከተራዘመው የኤል-ፋሸር ከበባ ለማምለጥ ሕዝቡ ወደዚያ ተሰዷል።
ኤጀንሲው በግጭቱ ውስጥ በተሳተፉት ሁሉም አካላት ፈቃድ ተሰጥቶት ሲጓዝ የነበረው የእርዳታ ኮንቮይ ላይ የተፈጸመው ይህ ጥቃት፣ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በሱዳን በእርዳታ ንብረቶቹ ላይ የተፈጸመ ስድስተኛው ከባድ ጥቃት በመሆኑ፣ አስቸኳይ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል። በእነዚህ ጥቃቶች በትንሹ ስምንት የሰብአዊ እርዳታ ሠራተኞች ተገድለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X