ኢትዮጵያ የአመጋገብ ደህንነትን ለማሳደግ የሚረዳ ብሔራዊ ዲጂታል የምግብ ንጥረ ነገር ይዘት ሰንጠረዥ ይፋ አደረገች
16:19 06.12.2025 (የተሻሻለ: 16:24 06.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የአመጋገብ ደህንነትን ለማሳደግ የሚረዳ ብሔራዊ ዲጂታል የምግብ ንጥረ ነገር ይዘት ሰንጠረዥ ይፋ አደረገች
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት ጋር በመተባበር ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ያልተሻሻለውን ይህን የቀድሞ በእጅ የሚሞላ ሠንጠረዥ ለመከለስ ሰፊ ጥናት አከናውኗል።
ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር የተገነባው ሰንጠረዡ ከ726 በላይ የምግብ አይነቶችን አካትቶ መያዙ ተጠቁሟል፡፡
የተሻሻለው የዳታቤዝ ሥርዓት ለጤና፣ ለአመጋገብ እና ለእርሻ ፕሮግራሞችና ፖሊሲዎች እንደ ወሳኝ ማስረጃ ምንጭ ሆኖ ለማገልገል ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ በመድረኩ ላይ ተገልጿል ሲሉ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia