ኡጋንዳ የራሷን የኮኮዋ ምርት ለማቀነባበር ተዘጋጅታለች ሲሉ ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ አስታወቁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኡጋንዳ የራሷን የኮኮዋ ምርት ለማቀነባበር ተዘጋጅታለች ሲሉ ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ አስታወቁ
ኡጋንዳ የራሷን የኮኮዋ ምርት ለማቀነባበር ተዘጋጅታለች ሲሉ ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ አስታወቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.12.2025
ሰብስክራይብ

ኡጋንዳ የራሷን የኮኮዋ ምርት ለማቀነባበር ተዘጋጅታለች ሲሉ ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ አስታወቁ

"ቡንዲቡግዮ ውስጥ የቸኮሌት ፋብሪካ እናቋቁማለን" ሲሉ ዮዌሪ ሙሴቬኒ የኮኮዋ ምርት በበዛበት ክልል ባደረጉት ጉብኝት ተናግረዋል። ይህም ፕሮጀክት ጥሬ ዕቃን ወደ ውጭ ከመላክ ይልቅ በአገር ውስጥ እሴት የመጨመር ወሳኝ ለውጥ መሆኑን አመላክተዋል።

ምንም እንኳን ባለፉት ጊዜያት ኡጋንዳ ወተትና ስኳር የመሳሰሉ አስፈላጊ ምርቶች የሏትም፤ በሚል ምክንያት ባለሀብቶችን ለመሳብ የተደረገው ሙከራ ባይሳካም፣ አሁን ላይ ግን የሚያለማ ባለሀብት እንደተገኘ ፕሬዝዳንቱ አሳውቀዋል።

በቡንዲቡግዮ ያለው የኮኮዋ ልማት ከ1990ዎቹ  ጀምሮ የቆየ ታሪክ ያለው ሲሆን ለግብርና-ኢንዱስትሪ ልማት ጥሩ መሠረት እንደሚሆን አጽንዖት ሰጥተዋል።

አዲሱ ፋብሪካ የሥራ ዕድል ይፈጥራል፣ ገበያዎችን ያሰፋል፣ እንዲሁም የቤተሰብ ገቢን ይጨምራል፣ ይህም ጥሬ ዕቃዎችን ወደ ውጭ ከመላክ ይልቅ በማቀነባበር ለዩጋንዳ ኢኮኖሚያዊ ራስን መቻል አስተዋጽኦ ያደርጋል ሲሉ ንግግራቸውን ደምድመዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0