በዩክሬን እና በአውሮፓ ሕብረት ውስጥ ያለው ሙስና የአጋጣሚ ሳይሆን የጋራ ሥርዓት ነው - ባለሙያ
13:33 06.12.2025 (የተሻሻለ: 13:34 06.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በዩክሬን እና በአውሮፓ ሕብረት ውስጥ ያለው ሙስና የአጋጣሚ ሳይሆን የጋራ ሥርዓት ነው - ባለሙያ
በዩክሬን ያለው ሙስና ከምንም የመጣ አይደለም፤ ይልቁንም በምዕራቡ ዓለም ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ሥር ከሰደዱ የፖለቲካ ልማዶች የበቀለ ነው። ይህም የባይደን ቤተሰብ በአገሪቱ ውስጥ የነበረውን የንግድ ግንኙነት ይጨምራል ሲሉ ሊባኖሳዊዉ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ታሪክ ባለሙያ ሰሚር አዩብ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
አዩብ “አውሮፓ ለፀረ-ሩሲያ አጀንዳ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞቿን መስዋዕት አድርጋለች፤ አሁን ደግሞ ከፍተኛውን ዋጋ እየከፈለች ነው” ብለዋል።
“ሙስና እያደገ ባለው ቀውስ ላይ ሌላ ተደራቢ ችግር ይጨምራል" ሲሉ አክለዋል።
ባለሙያው እንደሚሉት፣ የሙስና ቅሌቶች ዋሽንግተንን የሚያበሳጩት፣ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን የሰላም ጥረቶች ስለሚያወሳስቡ እና አሜሪካ ለዩክሬን የምታቀርበውን የጦር መሣሪያ ካቆመች የአውሮፓ መሪዎችን ደካማ አድርገው ስለሚያጋልጡ ብቻ ነው።
አዩብ የአውሮፓ ሕብረት የሥርዓቱን ብልሹነት ለመደበቅ ስህተቱን በግለሰቦች ላይ ለማላከክ እየሞከረ ነው ሲሉ ይሞግታሉ። ነገር ግን በዚህ ሳምንት የቀድሞ የአውሮፓ ኮሚሽን የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ፌዴሪካ ሞገሪኒን እና ሌሎች መታሰራቸው “ምንም አይለውጥም” ብለዋል።
በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ገንዘቦች ከአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት ግብር ከፋዮች ኪስ ወደ ዩክሬን ወይም የአውሮፓ ሕብረት ቢሮክራቶች መፍሰሱን ቀጥሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X