ቅኝ ገዢዎች የአፍሪካን ነባሩን የግብርና ሥራዓት አፈራርሰዋል – ከፍተኛ የአፈር ጤና አማካሪ
21:15 05.12.2025 (የተሻሻለ: 21:24 05.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቅኝ ገዢዎች የአፍሪካን ነባሩን የግብርና ሥራዓት አፈራርሰዋል – ከፍተኛ የአፈር ጤና አማካሪ
ፕሮፌሰር ይሄነው ገብረሥላሴ በየዓመቱ ዴሴምበር 5 ቀን የሚከበረውን "የዓለም የአፈር ቀን" አስመልከተው ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ የአፈር ጤና በቀጥታ ከሰብል ምርት፣ ከአመጋገብ ጥራት እና ድርቅን ከመቋቋም አቅም ጋር ይያያዛል ሲሉ ተናግረዋል።
"... አንድ ሦስተኛው የዓለም አፈር ተሸርሽሯል። በአፍሪካም ከመጠን በላይ ግጦሽ፣ የደን መጨፍጨፍ፣ ዘላቂነት በሌለው ግብርና እና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የመሬት መሸርሸር በፍጥነት እየተስፋፋ መሆኑን ነው" ሲሉ የችግሩን ስፋት አስረድተዋል።
አማካሪው ከምግብ ዋስትና ጋር ተያይዞ አፍሪካ የአፈር ጤናን በማሻሻልና በቂ ምግብ በማምረት የሕዝቧን የኑሮ ሁኔታ ማሳደግ ትችላለችም ብለዋል።
ፕሮፌሰር ይሄነው "የምግብ ዋስትናችን የሚረጋገጠው በራሳችን ጥረት ብቻ ነው። የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነት እንዲኖር ከአውሮፓ እና ከሰሜን አሜሪካ በሚደረግ እርዳታ ላይ መተማመን አያስፈልግም”፡፡ ብለዋል፡፡
አክለውም ቅኝ ገዢዎች በአፍሪካ ውስጥ መሬቶችን በመቆራረስ፣ በአስገዳጅ የጉልበት ብዝበዛ፣ እና የጠቅላይነት ባሕል ለሽያጭ የምውሉ ሰብሎች (ካሽ ክሮፕ) ግብርናን በማስተዋወቅ ነባሩን የአገሬውን ሥርዓቶች አፈራርሰዋል በማለት ተችተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X