የሩሲያ ኃይሎች በዶንቴስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ የቤዚሚያንኖዬን ሰፈር ነጻ ማውጣታቸውን የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ
20:26 05.12.2025 (የተሻሻለ: 20:34 05.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ ኃይሎች በዶንቴስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ የቤዚሚያንኖዬን ሰፈር ነጻ ማውጣታቸውን የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ
ሰፈሩ በሩሲያ ጦር ኃይሎች “ደቡብ” የውጊያ ቡድን ነጻ መውጣቱን መከላከያ ሚኒስቴሩ ገልጿል።
እንደ ሚኒስቴሩ፣ ባሳለፍነው ሳምንት የሩሲያ ወታደሮች በርካታ መንደሮችን ነጻ አውጥተዋል፡፡
▪ዶኔትስክ ሕዝባዊ ረፑብሊክ - ቤዚሚያንኖዬ፣ ክሊኖቮዬ እና ክራስኖአርሜይስክ፤
▪በካርኮቭ ክልል - ቮልቻንስክ፣
▪ዛፖሮዥዬ ክልል - ዘሌኒ ጋይ፣ ዶብሮፖልዬ እና ቼርቮኖዬ ይገኙበታል።
በተጨማሪም የመከላከያ ሚኒስቴር እንዳለው፣ ከኅዳር 2ዐ እስከ 26 ባለው ጊዜ ውስጥ የሩሲያ ኃይሎች የዩክሬን ጦር ኃይሎችን ወታደራዊ-ኢንዱስትሪ ተቋማትን እና የሚደግፏቸውን የኃይል ማመንጫ መሠረተ ልማቶች፣ የሚጠቀሙባቸውን የትራንስፖርት እና የአየር ማረፊያ ንብረቶችን፣ የድሮን ማምረቻ እና ማስወንጨፊያ ቦታዎችን፣ የጥይትና የነዳጅ ማከማቻዎችን እንዲሁም የጦሩ ልዩ ልዩ ክፍሎችን እና የውጭ ቅጥረኞችን ምሽጎች ላይ ጥቃት ፈፅመዋል።
የዩክሬን ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ዳራን በተመለከተ የስፑትኒክ አፍሪካን ዝርዝር ትንታኔ ያንብቡ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X