የቡርኪና ፋሶ ጠቅላይ ሚኒስትር በሰሃራ ትልቁ የባሕል ሁነት በሆነው የአየር ፌስቲቫል ለመሳተፍ ለመሳተፍ ኒጀር ገቡ
19:59 05.12.2025 (የተሻሻለ: 20:04 05.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የቡርኪና ፋሶ ጠቅላይ ሚኒስትር በሰሃራ ትልቁ የባሕል ሁነት በሆነው የአየር ፌስቲቫል ለመሳተፍ ለመሳተፍ ኒጀር ገቡ
የቡርኪና ፋሶ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በዋጣው መግለጫ፣ ሪምታልባ ዣን ኢማኑኤል ውድራኦጎ 17ተኛውን የፌስቲቫሉን ዝግጅት ለመካፈል ከፍተኛ የመንግሥት ልዑክን እየመሩ ስፍራው ላይ ተገኝተዋል።
በሰሜን ኒጀር ኢፈሯኔ ውስጥ በዛሬው ዕለት በሚካሄደው የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከኒጀር አቻቸው አሊ መሐማኔ ላሚን ዜይን ጋር በፌስቲቫሉ ይታደማሉ።
የቻድ፣ የሴኔጋል እና የማሊ ጠቅላይ ሚኒስትሮችም በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ይገኛሉ። ቻድ የዚህ ዓመት የፌስቲቫሉ የክብር እንግዳ ነች።
የ2025 የፌስቲቫሉ የመሪ ቃል፦ “የአገር ውስጥ ቱሪዝም እና የእደ ጥበብ ስራዎች ማስተዋወቅ፤ የብሔራዊ ሉዓላዊነት እና ጠንካራ ልማት መሠረት” የሚል ነው።
ፌስቲቫሉ እስከ እሑድ ድረስ ይቀጥላል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/5
© telegram sputnik_ethiopia

2/5
© telegram sputnik_ethiopia

3/5
© telegram sputnik_ethiopia

4/5
© telegram sputnik_ethiopia

5/5
© telegram sputnik_ethiopia
1/5
© telegram sputnik_ethiopia
2/5
© telegram sputnik_ethiopia
3/5
© telegram sputnik_ethiopia
4/5
© telegram sputnik_ethiopia
5/5
© telegram sputnik_ethiopia