ኢትዮጵያ በጃማይካ የሜሌሳ ወጀብ ያደረሰውን ጉዳት ገምግሞ አስፈላጊውን እርዳታ የሚያመቻች ልዑክ መላኳ ተዘገበ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በጃማይካ የሜሌሳ ወጀብ ያደረሰውን ጉዳት ገምግሞ አስፈላጊውን እርዳታ የሚያመቻች ልዑክ መላኳ ተዘገበ
ኢትዮጵያ በጃማይካ የሜሌሳ ወጀብ ያደረሰውን ጉዳት ገምግሞ አስፈላጊውን እርዳታ የሚያመቻች ልዑክ መላኳ ተዘገበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.12.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በጃማይካ የሜሌሳ ወጀብ ያደረሰውን ጉዳት ገምግሞ አስፈላጊውን እርዳታ የሚያመቻች ልዑክ መላኳ ተዘገበ

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ የተመራው ልዑክ በደሴቲቱ በተለይም የሜሌሳ ወጀብ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰባቸውን አካባቢዎችን ጎብኝቷል።

የኢትዮጵያን ልዑክ አመስግነው የተቀበሉት የጃማይካ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታ ሴናተር አብካ ፊትዝ-ሄንሊ፣ አገራቱ “የዘር ሐረግ እና የባሕል ቅርስን ጨምሮ የበለፀገ ታሪክ እና ጠንካራ አጋርነትን እንደሚጋሩ” ጠቁመዋል፡፡

አምባሳደር ብርሃኑ በበኩላቸው፣ በጃማይካ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው አጋርነት በመጪዎቹ ዓመታት የበለጠ እንደሚጠናከር አያጠራጥርም ሲሉ ያላቸውን መተማመን ገልጸዋል።

ሴናተር አብካ ፊትዝ-ሄንሊ፣ “ጃማይካ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ከሜሊሳ ተጽእኖ እንድናገግም በማሰብ ወደ ጃማይካ የልዑካን ቡድን ለመላክ ያሳለፉትን ውሳኔ በደስታ ተቀብላለች።” ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በአፄ ኃይለሥላሴ የልጅ ልጅ ልዑል ኤርሚያስ ሣሕለሥላሴ የተመሠረተው ሮያል ኢትዮጵያን ትረስት፣ ጃማይካ የምታደርገውን የማገገሚያ ጥረቶች ለመደገፍ የ5 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ልገሳ ማድረጉን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0