ኢትዮ ቴሌኮም “ታሪካዊ” ያለውን የማስተር ሰርቪስ የኮንትራት ስምምነት ከካሜሩኑ ካምቴል ጋር መፈራረሙን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮ ቴሌኮም “ታሪካዊ” ያለውን የማስተር ሰርቪስ የኮንትራት ስምምነት ከካሜሩኑ ካምቴል ጋር መፈራረሙን አስታወቀ
ኢትዮ ቴሌኮም “ታሪካዊ” ያለውን የማስተር ሰርቪስ የኮንትራት ስምምነት ከካሜሩኑ ካምቴል ጋር መፈራረሙን አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.12.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮ ቴሌኮም “ታሪካዊ” ያለውን የማስተር ሰርቪስ የኮንትራት ስምምነት ከካሜሩኑ ካምቴል ጋር መፈራረሙን አስታወቀ

እንደ ኢትዮ ቴሌኮም መግለጫ፣ በካሜሩን ያውንዴ ከተማ የተፈረመው ስምምነት የካምቴል (CAMTEL) የሥራ ኃላፊዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከኢትዮ ቴሌኮም የተመለከቱትን ተሞክሮ ወደ ካሜሩን ለመውሰድ ከነበራቸው ፍላጎት የመነጨ ነው።

በዚህም ስምምነት መሠረት ሁለቱ ኦፕሬተሮች፦

▫ በካሜሩን የፋይናንስ ተደራሽነትን የሚያረጋግጥ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ለማስፋፋት፣

▫ ብሔራዊ ክላውድ በመገንባት የመንግሥት አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ለማድረግ፣

▫ የሞባይል ኔትዎርክ ጥራትን ለማረጋገጥ፣

▫ የካምቴልን አሠራር በይበልጥ በማዘመን ደንበኛ ተኮር ባሕል ለመገንባት፣

▫ ለተቋማት ዲጂታል መፍትሄዎችን፣ የተጨማሪ እሴት እና የኢንተርኮኔክት አገልግሎቶችን በጋራ ለመተግበር ያስችላቸዋል፡፡

የኢትዮጵያው ኩባንያ፣ “ይህ ስምምነት በኩባንያችን የ‘ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028 ስትራቴጂ’ መሠረት፣ ድንበር ተሻጋሪ አገልግሎት በማቅረብና አኅጉራዊ ትብብርን በማጎልበት የዲጂታል አፍሪካን ጉዞ ለማፋጠን የሚያስችል ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።” ብሏል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
ኢትዮ ቴሌኮም “ታሪካዊ” ያለውን የማስተር ሰርቪስ የኮንትራት ስምምነት ከካሜሩኑ ካምቴል ጋር መፈራረሙን አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ
1/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
ኢትዮ ቴሌኮም “ታሪካዊ” ያለውን የማስተር ሰርቪስ የኮንትራት ስምምነት ከካሜሩኑ ካምቴል ጋር መፈራረሙን አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ
2/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
ኢትዮ ቴሌኮም “ታሪካዊ” ያለውን የማስተር ሰርቪስ የኮንትራት ስምምነት ከካሜሩኑ ካምቴል ጋር መፈራረሙን አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ
3/3
1/3
2/3
3/3
አዳዲስ ዜናዎች
0