አሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት ዶዶማ የቀደመ የጣልቃገብነትን ወቀሳን ችላ ብለው ታንዛኒያ ላይ አዲስ ትችት ሰነዘሩ
16:38 05.12.2025 (የተሻሻለ: 16:44 05.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት ዶዶማ የቀደመ የጣልቃገብነትን ወቀሳን ችላ ብለው ታንዛኒያ ላይ አዲስ ትችት ሰነዘሩ
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴ ታንዛኒያ የነጻነት ጥሰቶችን ፈጽማለች እንዲሁም በሲቪሎች ላይ ኃይል ተጠቅማለች በማለት፣ ከታንዛኒያ ጋር ያለውን ግንኙነት ላይ “ሁሉን አቀፍ ግምገማ” እንደሚያደርግ አስታውቋል።
አስራ ስድስት የአውሮፓ ሕብረት አገራት በታንዛኒያ የድህረ-ምርጫ ሁኔታ ላይ የተሰማቸውን “ጥልቅ ስጋት” ገልጸው፤ ታንዛኒያ “በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሕግ ያለውን ግዴታ እንድታከብር” ጥሪ አቅርበዋል።
ቀደም ሲል፣ የታንዛኒያ መንግሥት ምዕራባውያን አገራት በውስጥ ጉዳዮቿ ጣልቃ መግባታቸውን፣ የአውሮፓ ሕብረት የታንዛኒያ ይፋዊ ተሳትፎ በሌለበት በአገሪቱ ያለውን ሁኔታ ላይ ለመወያየት መወሰኑን በመጠቅስ፣ በፅኑ ማውገዙ ይታወሳል።
ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሐሰን የጥቅምት 19 ሁከት መንግሥትን በኃይል ለመገልበጥ የተደረገ ሙከራ አካል እንደሆነ ተናግረዋል። የኃይል አጠቃቀሙም ከተጋረጠው ስጋት ደረጃ ጋር ተመጣጣኝ እንደነበር እና ዜጎችን ለመጠበቅ እንዲሁም አገራዊ መረጋጋትን ለማስጠበቅ ታስቦ እንደነበር አፅንዖት ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X