የአፍሪካ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ለደቡብ ሱዳን–ኢትዮጵያ-ጅቡቲ ምዕራፍ 2 የትራንስፖርት ኮሪደር 214.4 ሚሊዮን ዶላር አፀደቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአፍሪካ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ለደቡብ ሱዳን–ኢትዮጵያ-ጅቡቲ ምዕራፍ 2 የትራንስፖርት ኮሪደር 214
የአፍሪካ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ለደቡብ ሱዳን–ኢትዮጵያ-ጅቡቲ ምዕራፍ 2 የትራንስፖርት ኮሪደር 214 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.12.2025
ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ለደቡብ ሱዳን–ኢትዮጵያ-ጅቡቲ ምዕራፍ 2 የትራንስፖርት ኮሪደር 214.4 ሚሊዮን ዶላር አፀደቀ

ከአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን የተቀናሽ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ልዩ አቅርቦት የገንዘብ ድጋፍ የሚከተሉትን ድጎማዎችን አጽድቋል፦

ለኢትዮጵያ 181.5 ሚሊዮን ዶላር፣

ለጅቡቲ 29.71 ሚሊዮን ዶላር እና

ለደቡብ ሱዳን 1.96 ሚሊዮን ዶላር መድቧል።

የፕሮጀክቱ ምዕራፍ ሁለት በሦስቱም አገራት ዋና ዋና የመሠረተ ልማት ማሻሻያዎችን እንደሚኖሩት የተገለፀ ሲሆን በዚህም፦

ኢትዮጵያ ውስጥ የ67 ኪሜ የፍጥነት መንገድ ግንባታ እና የዲጂታል የትራንስፖርት ሥርዓቶች ማስፈፀምን ያካትታል።

በጅቡቲ በ18 ኪሜ የድኪል-ሙሉድ ክፍል (መስመር) ማሻሻያ ላይ ያተኩራል።

በደቡብ ሱዳን የ280 ኪሜ የካፖዬታ-ቦማ-ራአድ መንገድን ለማሻሻል የሚያስፈልጉ ጥናቶችን የማዘመን ሥራ ትሠራለች።

በተጨማሪም፣ በኢትዮጵያ 50 እና በጅቡቲ 15 ኪሎ ሜትሮች ተለዋጭ መንገዶች የማሻሻያ የፕሮጀክቱ አካል መሆናቸውንም ባንኩ በድረ-ገፁ አስታውቋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0