የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከል ማዕከል የቲቢ ሕክምናን በአጭር የሞባይል የጽሑፍ መልዕክት ለማሻሻል ያለመ አዲስ ጥናት እያካሄደ እንደሚገኝ አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከል ማዕከል የቲቢ ሕክምናን በአጭር የሞባይል የጽሑፍ መልዕክት ለማሻሻል ያለመ አዲስ ጥናት እያካሄደ እንደሚገኝ አስታወቀ
የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከል ማዕከል የቲቢ ሕክምናን በአጭር የሞባይል የጽሑፍ መልዕክት ለማሻሻል ያለመ አዲስ ጥናት እያካሄደ እንደሚገኝ አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.12.2025
ሰብስክራይብ

የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከል ማዕከል የቲቢ ሕክምናን በአጭር የሞባይል የጽሑፍ መልዕክት ለማሻሻል ያለመ አዲስ ጥናት እያካሄደ እንደሚገኝ አስታወቀ

ጥናቱ ከፍተኛ የቲቢ (የሳንባ ነቀርሳ) ስርጭት ባለባቸው ኢትዮጵያና ላይቤሪያ እየተሠራ እንደሆነም ገልጿል፡፡ በአገራቱ በሽታው በግምት በ100 ሺህ ሕዝብ በቅደም ተከተል 119 እና 308 ሰዎች ይያዛሉ።

ይህንን የማያቋርጥ ፈተና ለመቅረፍ የአፍሪካ ሲዲሲ ጥናት የሞባይል ቴክኖሎጂን እንደ ተጨባጭ መፍትሄ እየተጠቀመ ነው።

“... አጭር የሞባይል መልዕክቶችን በመጠቀም የቲቢ ታካሚዎችን ሕክምናቸውን ለማስታወስ፣ እንቅፋቶችን ለመለየት እና በታካሚዎች ውጤት ላይ ያላቸውን ተፅእኖ በመገምገም የቲቢ ሕክምናን ለማሻሻል ያለመ ነው፡፡” ሲል ማዕከሉ አስታውቋል።

የጥናት ሥራው ከአገራቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴሮችና ዩኒቨርስቲዎች ጋር በማዕከሉ የቴክኒክ ኋላፊነት እየተከወነ ሲሆን ታህሳስ 3 እንደሚጠናቀቅ ይፋ ተደርጓል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0