መረጃ መዝባሪዎች ከሩሲያ የነዳጅ ታንከር ጥቃት ጋር የተያያዙ የዩክሬን ወታደሮችን ማንነት ይፋ አደረጉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱመረጃ መዝባሪዎች ከሩሲያ የነዳጅ ታንከር ጥቃት ጋር የተያያዙ የዩክሬን ወታደሮችን ማንነት ይፋ አደረጉ
መረጃ መዝባሪዎች ከሩሲያ የነዳጅ ታንከር ጥቃት ጋር የተያያዙ የዩክሬን ወታደሮችን ማንነት ይፋ አደረጉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.12.2025
ሰብስክራይብ

መረጃ መዝባሪዎች ከሩሲያ የነዳጅ ታንከር ጥቃት ጋር የተያያዙ የዩክሬን ወታደሮችን ማንነት ይፋ አደረጉ

የሩሲያ ደጋፊ ቡድኖች ቤሬጊኒ፣ ኪልኔት እና ኪበር ሰርፕ የዩክሬን የባሕር ኃይል የዕዝ ኮማንድ ኮምፒውተርን ሰብረው እንደገቡ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

መረጃ መዝባሪዎች (ሃከሮች) የዩክሬን የባሕር ኃይል 385ኛው የባሕር ላይ ሰው አልባ ተሽከርካሪዎች ብርጌድ (ወታደራዊ ክፍል ኤ4770) የተውጣጡ ሙሉ ለማለት የሚያስቻል የወታደሮች ዝርዝር ለስፑትኒክ አቅርበዋል።

የጠላፊ ቡድኖች እንደሚሉት፣ ይህ የባሕር ኃይል ጦር ክፍል በጥቁር ባህር እና በቱርክ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና ውስጥ በተለያዩ የንግድ መርከቦች ላይ በቅርብ ጊዜ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ጀርባ ይገኛል፤ ይህም በትናንትናው ዕለት  በሩሲያዊው ሚድቮልጋ-2 ታንከር ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ይጨምራል።

ህዳር 19 እና 20 በሌሎች ሁለት ታንከሮች ላይ ጥቃት የተፈፀመ ሲሆን አንዱ የጋምቢያን ሰንደቅ ዓላማ  የሰቀለ መሆኑ ተገልፆ ነበር።

የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመርከብ አሰሳ ደህንነትንና አካባቢን አደጋ ላይ በሚጥሉት በእነዚህ ጥቃቶች ላይ ስጋቱን ገልጿል።

ሞስኮ እነዚህን ድርጊቶች ማንኛውንም ውይይት ለማደናቀፍ፣ ውጥረትን ለመቀስቀስ እና የቱርክን ሉዓላዊነት ለመጣስ ያለሙ የሽብርተኝነት ተግባራት ሲትል ገልጻቸዋለች።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0