የጋና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በመገናኛ ብዙኃን ትብብር ላይ በተካሄደ "የስፑትኒክፕሮ" ስብሰባ ላይ ተሳተፉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየጋና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በመገናኛ ብዙኃን ትብብር ላይ በተካሄደ "የስፑትኒክፕሮ" ስብሰባ ላይ ተሳተፉ
የጋና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በመገናኛ ብዙኃን ትብብር ላይ በተካሄደ የስፑትኒክፕሮ ስብሰባ ላይ ተሳተፉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.12.2025
ሰብስክራይብ

  የጋና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በመገናኛ ብዙኃን ትብብር ላይ በተካሄደ "የስፑትኒክፕሮ" ስብሰባ ላይ ተሳተፉ

በጋና በሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ እና በጋና-ሩሲያ የንግድና ግንኙነት ማዕከል  ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ይህ ዝግጅት፣ ዕውቀትን ለመለዋወጥ፣ ሐሳቦችን ለመፍጠር እና በሁለቱ አገሮች መካከል ባሉ የመገናኛ ብዙኃን ድርጅቶች መካከል ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር ጠቃሚ ዕድል ፈጥሯል።

የሮሲያ ሴጎድኒያ ዓለም አቀፍ ትብብር ዳይሬክተር ቫሲሊ ፑሽኮቭ እንደተናገሩት፣ ድንበር ተሻጋሪ የሚዲያ ትብብር አሳታፊ፣ ዘርፈብዙ፣ ዘመናዊና፣ የተለያዩ ይዘቶች ያላቸው ፕሮግራሞች ለህዝብ ማቅረባቸው የሚዲያ ማዕቀፉን ለማስፋፋት ወሳኝ ናቸው።

በጋና የሩሲያ ኤምባሲ አማካሪ ናታሊያ ሙዠኒኮቫ እንደገለጹት፣ "ጋዜጠኞች መረጃን የሚያቀርቡበት መንገድ የሩሲያ-አፍሪካ ግንኙነት በእውነት ላይ ወይም በተሳሳተ መንገድ እንደሚታይ በማሳየት ረገድ ሚና ወሳኝ አለው።"

የሀገራቱ የትብብር ማዕከል የንግድ ልማትና ፈጠራ ኃላፊ ዢዮና አዮርኮር ሆልም እንደገለጹት፣ በመገናኛ ብዙኃን ትብብር ማለት እያንዳንዱ የመገናኛ ብዙኃን ጥንካሬውን መረዳት፣ ክህሎቶችን መጋራት፣ በጋራ መማር እንዲሁም በውይይቶችና በሰርቶ ማሳያዎች አማካኝነት የትርክትን ወሰንን ማራዘም ማለት ነው።

ስብሰባው ከፍተኛ ተሳትፎን የነበረበት ሲሆን፣ የጋና ጋዜጠኞች የሩሲያ ጋዜጠኝነት ልዩ ባህርያትና የጋራ የሥራ ዕድሎችን በተመለከተ በርካታ ጥያቄዎችን አንስተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0