የኢትዮጵያ መንግሥት የግብጽ ባለሥልጣናትን ቀጣናውን በማተራመስ ከሰሰ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ መንግሥት የግብጽ ባለሥልጣናትን ቀጣናውን በማተራመስ ከሰሰ
የኢትዮጵያ መንግሥት የግብጽ ባለሥልጣናትን ቀጣናውን በማተራመስ ከሰሰ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.12.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ መንግሥት የግብጽ ባለሥልጣናትን ቀጣናውን በማተራመስ ከሰሰ

የግብጽ ባለሥልጣናት ተደጋጋሚ መግለጫዎች፣ የቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነቶችን በመጥቀስ "ታሪካዊ መብቶች" ላይ መተማመናችውን የሚያሳይ ነው ሲል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ኮንኗል፡፡

"ካይሮ ፍላጎቷን የሚያሟሉ ተገዥ፣ ደካማና የተከፋፈሉ ደንበኛ ሀገራት እንዲኖሩ በማሰብ፣ ባለሥልጣናቱ ትኩረቱን በኢትዮጵያ ላይ ብቻ ያልተገደበ የአፍሪካ ቀንድን የማተራመስ ዘመቻ እያካሄዱ ነው.... ኢትዮጵያን በፍጹም ሊያስፈራራት ያልቻለውን ይህን ያረጀ አሠራር የምንሰናበትበት ጊዜ አሁን ነው" ሲል ሚኒስቴሩ ፀብ አጭሪ ያለውን የግብፅ እንቅስቃሴ ክፉኛ ተችቷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ በድንበሯ ውስጥ የሚገኙትን የተፈጥሮ ሀብቶቿን ለመጠቀም ከማንም ፈቃድ የመጠየቅ ግዴታ እንደሌለባት ነው የገለፀው፡፡

“ከኢትዮጵያ ደጋማ ቦታዎች የሚመነጨው አባይ ወንዝ፣ የናይል ተፋሰስን 86 በመቶ ውሃ ያዋጣዋል። የአባይ ተፋሰስ ውሃ የኢትዮጵያ 70 በመቶ የገጸ ምድር ውሃ ነው፡፡ ኢትዮጵያ እንደሌሎቹ ሁሉም የተፋሰሱ አገራት ሁሉ፣ ይህንን የተፈጥሮ ሃብት የመጠቀም መብት አላት። በዚህ ዐውድ ውስጥ ፍትሐዊ፣ ምክንያታዊ እና ተመጣጣኝ አጠቃቀም ተፈጻሚነት ያለው የዓለም አቀፍ ሕግ አምድ የሆነ መርህ ነው።”

ቀድም ሲል በግትርነት መፍትሔዎችን ስታስተጓጉል የነበረችው ግብፅ አሁን ላይ በይፋ ለድርድሩ እምቢተኛ መሆኗን አሰታወቃለች ሲል ሚኒስቴሩ አስረድቷል።

ግብጽ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጀመር፣ በሀገሪቱ የውሃ እጥረት እንደሚያስከትልፅ ስጋቷን ገልጻለች። በሌላ በኩል የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የትልቅ መሠረተ ልማት ፕሮጀክት ገቢራዊነት የታችኛው የናይል ወንዝ ሀገራትን እንደማይጎዳ በተደጋጋሚ አሳስበዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0