የኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ ተጠቃሚ አካውንቶች 136 ሚሊዮን ደረሱ፤ ዓመታዊ ዲጂታል ግብይትም ከ9.6 ትሪሊዮን ብር ተሻግሯል

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ ተጠቃሚ አካውንቶች 136 ሚሊዮን ደረሱ፤ ዓመታዊ ዲጂታል ግብይትም ከ9
የኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ ተጠቃሚ አካውንቶች 136 ሚሊዮን ደረሱ፤ ዓመታዊ ዲጂታል ግብይትም ከ9 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.12.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ ተጠቃሚ አካውንቶች 136 ሚሊዮን ደረሱ፤ ዓመታዊ ዲጂታል ግብይትም ከ9.6 ትሪሊዮን ብር ተሻግሯል

ይህ ከፍተኛ የዲጂታል ግብይት ዕደገት በመደበኛው የባንክ ሥርዓት ውስጥ ከታየው መጠነ-ሰፊ ዕድገት ጋር የሚጣጠም ነው መሆኑን ባለሥልጣናትን ጠቅሶ የአገር ውስጥ የግል ሚዲያ ዘግቧል፡፡  በ2020 ከ1 ሚሊዮን በታች የነበሩት የሞባይል ገንዘብ አካውንቶች በ2025 ወደ 136 ሚሊዮን መወንጨፋቸውን ዘገባው ጠቁሟል፡፡

በሚዲያው ዋቢ የተደረገው የብሔራዊ መረጃ እንደሚያሳየው ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ፦

🟠 የባንኮች ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ ከ1.04 ትሪሊዮን ብር ወደ 3.55 ትሪሊዮን ብር አድጓል።

🟠 የተሰጠ ጠቅላላ ብድር ከ559 ቢሊዮን ብር ወደ 3.24 ትሪሊዮን ብር ከፍ ብሏል።

🟠 ከወለድ ነፃ የፋይናንስ አገልግሎት ተቀማጭ ገንዘብ 425 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡ 

🟠 የተካፉል ኢንሹራንስ ክፍያዎች በጠቅላላው 471 ሚሊዮን ብር ሆኗል።

በ2021 የተጀመረው ሁለተኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፋይናንስ ተደራሽነት ስትራቴጂ፤ በ2020 የነበረውን 45 በመቶ የአዋቂዎች መደበኛ አካውንት ባለቤትነት እ.ኤ.አ. በ2025 ወደ 70 በመቶ ከፍ ለማድረግ ያለመ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0