- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

ዩኒቨርሲቲ መግባት ብቸኛ አማራጭ ነውን? ሀገር ያፈራቻቸው ሌሎች ዕድሎችን እንዴት እንጠቀም?

ዩኒቨርሲቲ መግባት ብቸኛ አማራጭ ነውን? ሀገር ያፈራቻቸው ሌሎች ዕድሎችን እንዴት እንጠቀም?
ሰብስክራይብ

“ቴክኒክ እና ሙያ መግባት ማለት ከዩኒቨርሲቲ ያነሰ ተደርጎ ነው ትርጉም የተወሰደው። ምክንያቱም ይሄ እንደ ዲፕሎማ ነው የሚቆጠረው። ያኛው እንደ ዲግሪ ስለሚቆጠር እና ማሻሻል ይፈልጋል። ይሄ የዩኒቨርሲቲ ባህሪ ኖሮት ሌላ ደረጃዎች ተቀምጦለት ኢላማ( ግቡም) ተቀይሮ ነው መምጣት ያለበት።” ሲሉ የስነ-አዕምሮ ባለሙያ እና አማካሪ አቶ እድሜአለም ግዛ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ የስነ-አዕምሮ ባለሙያ እና አማካሪ ከሆኑት አቶ እድሜአለም ግዛ ጋር በመሆን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ጋር ተያይዞ ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ የተቆረጠውን ውጤት የማያስመዝገቡ ተማሪዎች ቁጥር እየላቀ መምጣቱን ተከትሎ እነኚህ ተማሪዎች እንዴት ባለ መልኩ አእምሯቸውን አዘጋጅተው ሌሎቸ አማራጮችን መመልከት አለባቸው በሚለው ጉዳይ ተወያይተናል፡፡

በዚሁ መሰናዶ ሁለተኛ ክፍል ደግሞ በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ እና በሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎቸ መካከል በቋንቋ እና ባህል ረገድ ስለተመሰረተው ግኑኝነት በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ መምህር እና በዩኒቨርሲቲው ስር ያለው የአለቃ ገብረሃና የባህል ጥናት እና ልማት ዳይሬክተር ከሆኑት ከአቶ መሰረት ወርቁ ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0