ምዕራባውያን የሚሰብኩትን አይኖሩም - ጠበቃ እና የዓለም አቀፍ ሕግ ባለሙያ

ሰብስክራይብ

ምዕራባውያን የሚሰብኩትን አይኖሩም - ጠበቃ እና የዓለም አቀፍ ሕግ ባለሙያ

ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ በምዕራባዊያን ኃያላን ሀገራት የተፈጸሙ ወንጀሎችን ለመመርመር ያደረጋቸው ጥቂት ሙከራዎች በማስፈራሪያዎች መቋረጣቸውን አንዷለም በውቀቱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል፡፡

"የሶሪያ፣ ኢራቅ እና አፍጋኒስታን ጉዳዮች በአሜሪካ ቀጥተኛ ተሳትፎ ተቋርጠዋል፡፡ በተመሳሳይ ፍርድ ቤቱ ዩናይትድ ኪንግደም በሶሪያ እና ኢራቅ ላይ ያላትን ተሳትፎ አስመልክቶ የጀመረው ምርመራም ቆሟል፡፡ ምክንያቱን ብትጠይቃቸው አሳማኝ መልስ አይሰጡህም። ምዕራባዊያን ሁልጊዜ ጣምራ መለኪያ ነው የሚጠቀሙት" ብለዋል፡፡

ጠበቃው የደቡቡ ዓለም ምዕራባዊያን በፍርድ ቤቱ እና በሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ላይ የሚፈጽሟቸውን ኢ-ፍትሐዊ አሠራሮች እንዲያርሙ መሥራት እንዳለበትም አመላክተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0