ከአውሮፓ የሚገቡ ፀረ-ተባይ መድኃኒቶች ማህበረሰብ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ የእጀ አዙር ቅኝ አገዛዝ አዝማሚያዎች ናቸው - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱከአውሮፓ የሚገቡ ፀረ-ተባይ መድኃኒቶች ማህበረሰብ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ የእጀ አዙር ቅኝ አገዛዝ አዝማሚያዎች ናቸው - ባለሙያ
ከአውሮፓ የሚገቡ ፀረ-ተባይ መድኃኒቶች ማህበረሰብ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ የእጀ አዙር ቅኝ አገዛዝ አዝማሚያዎች ናቸው - ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.12.2025
ሰብስክራይብ

ከአውሮፓ የሚገቡ ፀረ-ተባይ መድኃኒቶች ማህበረሰብ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ የእጀ አዙር ቅኝ አገዛዝ አዝማሚያዎች ናቸው - ባለሙያ

አውሮፓውያን የማያቋርጥ ችግሮችን ወደ አፍሪካ ሀገራት በማስገባት ልመና፣ ራስን አለመቻል እና ተገዢነትን በማስረጽ ወደ ዘመናዊ ቅኝ አገዛዝ የመግባት አዝማሚያ እያራመዱ ይገኛል ሲሉ የሰብል ጥበቃ ከፍተኛ ባለሙያ ታደሰ ፈቃደ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

“በዘንድሮ ዓመት እንኳን ጊዜ ያለፈበት የአፈር ማዳበሪያ ገብቶ ነበር፡፡ ያ አንድ አካባቢን ይበክላል፣ ሁለተኛ መሬቱ ምርታማ አይሆንም፣ ምርታማ አልሆነም ማለት ሰው ወደ ተረጂነት ይሄዳል፡፡ ከኬሚካሉም አንጻር አካባቢውም እየተበከለ ነው፡፡ በቀጥታም በተዘዋዋሪም ማህበረሰቡ ላይ ጉዳት አለው፡፡ ያ ማለት ደግሞ ሰው ራሱን እንዳይችል ዞሮ ዞሮ የእነሱ ጥገኛ እንዲሆን ያደርጋል” ሲሉ አስረድተዋል፡፡

መድኃኒቶች፣ ኬሚካሎችና መሰል ምርቶች ግዜ ያለፈባቸው አልያም አካባቢን ሊበክሉ የሚችሉ ሆነው እያለ የራሳቸው ተልዕኮ ኖሯቸው ተደራሽ እንደሚደረጉ ባለሙያው አንስተዋል፡፡

"የተለያዩ ኬሚካሎች ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ ሼልፍ ላይፍ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ አሁን ላይ ግን ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ ያሉት አንድ ዓመት እና ከዛ በታችም አገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈ፣ ሊያልፍ የተቃረበ መድኃኒት እና ኬሚካሎች ናቸው።"

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0