ማዳጋስካር የቀድሞውን ፕሬዝዳንት አንድሪ ራጆሊናን ልትከስ መሆኑ ተገለፀ
17:06 02.12.2025 (የተሻሻለ: 17:14 02.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ማዳጋስካር የቀድሞውን ፕሬዝዳንት አንድሪ ራጆሊናን ልትከስ መሆኑ ተገለፀ
አዲሱ የፍትሕ ሚኒስትር ፋኒሪሶአ ኤርናይቮ፤ የቀድሞው ሀገር መሪ በውጭ ሀገር ስለሚገኙ፤ ዓለም አቀፍ የእስር ማዘዣ እንዲወጣ መታሰቡን ለውጭ ሚዲያ ገልፀዋል።
የቀድሞውን ፕሬዝዳንትን ጨምሮ በየትኛውም ወንጀል የተጠረጠረ ማንኛውም ሰው ለሕግ ሂደት ተገዢ እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
ሕጋዊ እርምጃው ራጆሊና ለብዙ ሳምንታት ከዘለቁ ተቃውሞዎች በኋላ ከሀገር መውጣታቸውን ተከትሎ በማዳጋስካር የፖለቲካ ሽግግር እየተደረገ ባለበት ወቅት የመጣ ነው።
ሆኖም የቀድሞው ፕሬዝዳንት የፈረንሳይ ዜጋ በመሆናቸው የሕግ ሂደቱን ሊያወሳስብ ይችላል ተብሏል።
እንደ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ የቀድሞው መሪ ጥቅምት 2 ቀን በፓሪስ ድጋፍ በፈረንሳይ አውሮፕላን ማዳጋስካርን ለቀው ወጥተዋል። የሚገኙበት ቦታ አሁንም ግልጽ ባይሆንም አንዳንድ መገናኛ ብዙኃን ገንዘባቸውን ከሚያስቀምጡባት ዱባይ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቅሰዋል። ይሁን እንጂ እስካሁን የት እንዳሉ የሚገልፅ ይፋዊ መረጃ የለም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X