ብሔራዊ ፓርኮች ሰፊ የመሠረተ ልማት ክፍተት እንዳለባቸው የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በጥናቱ አረጋገጠ
20:44 01.12.2025 (የተሻሻለ: 20:54 01.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ብሔራዊ ፓርኮች ሰፊ የመሠረተ ልማት ክፍተት እንዳለባቸው የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በጥናቱ አረጋገጠ
ከ2014–2017 በተካሄደ የኦዲት ጥናት በዋና ዋና ፓርኮች እና የቱሪስት መዳረሻዎች መንገዶች፣ ኤሌክትሪክ፣ ውሃ፣ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶች፣ ማረፊያ ቦታዎች እና መሠረታዊ አገልግሎቶች የተበላሹ፣ ያልተሟሉ አልያም ሙሉ በሙሉ የሌሉ ሆኖ መገኘቱ ይፋ ተደርጓል።
ከሰሜን እና ባሌ ብሔራዊ ፓርኮች በስተቀር ሌሎቹ አስራ አንድ ፓርኮች መሠረታዊ የመሠረተ ልማት እና አጠቃላይ የአስተዳደር ዕቅዶች የሌላቸው አልያም በአግባቡ ያልተተገብሩ ሆነው መገኘታቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ሪፖርቱን ጠቅሶ ዘግቧል።
በጥናቱ መሠረት የቱሪስት መዳረሻ መሠረተ ልማት ያልተሟላላቸው፦
የአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ፣
የገራሌ ብሔራዊ ፓርክ፣
የአብያታ-ሻላ ሐይቆች ብሔራዊ ፓርክ፣
የሰንቀሌ ቆርኪዎች መጠለያ ስፍራ ተጠቅሰዋል።
የኦዲት ሪፖርቱ ዋነኛ ችግር አድርጎ የጠቀሳቸው፦
የቱሪዝም ሚኒስቴር ለቱሪስት ስፍራዎች አነስተኛውን የመሠረተ ልማት ደረጃዎች አለመወሰኑ፣
የቁጥጥር ማዕቀፎች ማነስ እና የዕቅድ እጥረቶች፣
ፓርኮቹ ያለ ዕቅድ ወይም ደካማ አተገባበር መሥራታቸው።
“በመሠረታዊ የመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ ማሻሻያ እና ኢንቨስት ካልተደረገ፤ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ዘርፍ የሥራ ዕድል የመፍጠር፣ ኢንቨስትመንት የመሳብ እና የውጭ ምንዛሪ የማምጣት ግቡን ማሳካት እንደማይችል” ሪፖርቱ አስጠንቅቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X