https://amh.sputniknews.africa/20251201/2371773.html
ኢትዮጵያ የሳታላይት ዳታን ያለማቋረጥ የሚቀበል ቴክኖሎጂ አስጀመረች
ኢትዮጵያ የሳታላይት ዳታን ያለማቋረጥ የሚቀበል ቴክኖሎጂ አስጀመረች
Sputnik አፍሪካ
ኢትዮጵያ የሳታላይት ዳታን ያለማቋረጥ የሚቀበል ቴክኖሎጂ አስጀመረች ቴክኖሎጂው በቋሚነት መሬት ላይ የሚተከልና የአንድን ቦታ መገኛ ከጂ.ፒ.ኤስ በመቀበል ከፍተኛ ጥራት ያለው መረጃ የሚሰጥ መሆኑን የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር... 01.12.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-12-01T19:24+0300
2025-12-01T19:24+0300
2025-12-02T13:54+0300
sputnik africa
telegram sputnik_ethiopia
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07e9/0c/02/2379375_0:0:800:450_1920x0_80_0_0_164a7abaa7dc6e1e80cf7f2350d9bed3.jpg
ኢትዮጵያ የሳታላይት ዳታን ያለማቋረጥ የሚቀበል ቴክኖሎጂ አስጀመረች ቴክኖሎጂው በቋሚነት መሬት ላይ የሚተከልና የአንድን ቦታ መገኛ ከጂ.ፒ.ኤስ በመቀበል ከፍተኛ ጥራት ያለው መረጃ የሚሰጥ መሆኑን የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ ተናግረዋል፡፡“ይህ የቦታ አሁናዊ መገኛ አመልካች ቴክኖሎጂ የቅየሳ ሞያተኞች፣ ተመራማሪዎች፣ የአደጋ ተንታኞች፣ የመልክዓምድር እና የልዩ አገልግሎት ካርታ የሚያዘጋጁ ሞያተኞች ሥራ በሚሠሩበት ወቅት የያዙት ተንቀሳቃሽ የጂ.ፒ.ኤስ መሳሪያ የቆሙበት ቦታ መገኛን በሳንቲ ሜትር ደረጃ መረጃ የሚሰጥ ነው” ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡የቴክኖሎጂው ተጨማሪ አገልግሎቶች፦ ግድቦችን መገንባትና ደህንነታቸውን መከታተል፣ የመሬት አስተዳደር አሠራርን ማሻሻል፤ የሎጂስቲክስ ስርዓቱን ማሳለጥ፣ ልዩ ልዩ መሠረተልማቶችን ማስፋፋት፣ ግብርናንና የማዕድን ዘርፉን ማዘመን፡፡ ቴክኖሎጂው የቅየሳ ሥራ ለመሥራት መነሻ የሚሆኑ ተጨማሪ የጂ.ፒ.ኤስ መሳሪያዎች መትከል የግድ የነበረውን አሠራር ያስቀረ ነው ተብሏል፡፡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2025
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07e9/0c/02/2379375_100:0:700:450_1920x0_80_0_0_02a2ce4c2f215434fd283dbb5332c20c.jpgSputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
ኢትዮጵያ የሳታላይት ዳታን ያለማቋረጥ የሚቀበል ቴክኖሎጂ አስጀመረች
19:24 01.12.2025 (የተሻሻለ: 13:54 02.12.2025) ኢትዮጵያ የሳታላይት ዳታን ያለማቋረጥ የሚቀበል ቴክኖሎጂ አስጀመረች
ቴክኖሎጂው በቋሚነት መሬት ላይ የሚተከልና የአንድን ቦታ መገኛ ከጂ.ፒ.ኤስ በመቀበል ከፍተኛ ጥራት ያለው መረጃ የሚሰጥ መሆኑን የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ ተናግረዋል፡፡
“ይህ የቦታ አሁናዊ መገኛ አመልካች ቴክኖሎጂ የቅየሳ ሞያተኞች፣ ተመራማሪዎች፣ የአደጋ ተንታኞች፣ የመልክዓምድር እና የልዩ አገልግሎት ካርታ የሚያዘጋጁ ሞያተኞች ሥራ በሚሠሩበት ወቅት የያዙት ተንቀሳቃሽ የጂ.ፒ.ኤስ መሳሪያ የቆሙበት ቦታ መገኛን በሳንቲ ሜትር ደረጃ መረጃ የሚሰጥ ነው” ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡
የቴክኖሎጂው ተጨማሪ አገልግሎቶች፦
ግድቦችን መገንባትና ደህንነታቸውን መከታተል፣
የመሬት አስተዳደር አሠራርን ማሻሻል፤
የሎጂስቲክስ ስርዓቱን ማሳለጥ፣
ልዩ ልዩ መሠረተልማቶችን ማስፋፋት፣
ግብርናንና የማዕድን ዘርፉን ማዘመን፡፡
ቴክኖሎጂው የቅየሳ ሥራ ለመሥራት መነሻ የሚሆኑ ተጨማሪ የጂ.ፒ.ኤስ መሳሪያዎች መትከል የግድ የነበረውን አሠራር ያስቀረ ነው ተብሏል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X