የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ኢ-ፍትሐዊ አሠራሮች ሊታረሙ ይገባል - የሕግ ባለሙያ

ሰብስክራይብ

የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ኢ-ፍትሐዊ አሠራሮች ሊታረሙ ይገባል - የሕግ ባለሙያ

ፍርድ ቤቱ የሃያላን ሀገራት ግዙፍ የመብት ጥሰቶችን በተለየ መንገድ እንደሚመለከት የሕገ-መንግሥት እና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ዳይሬክተር ኃይለየሱስ ታዬ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል፡፡

ኃላፊው ፍርድ ቤቱ በአፍሪካ ጉዳዮች ከመጠመድ ወጥቶ ሁሉንም የዓለም ሀገራት እኩል ሊያገለግል እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

"በኢኮኖሚ ያደክ ሀገር ካልሆንክ ፍርድ ቤቱ የመጨረሻ መዳረሻህ መሆኑ እርግጥ ነው። ግዙፍ የመብት ጥሰቶችን የሚፈጽሙ ታላላቅ መንግሥታትን ግን ማንም አይጠይቃቸውም። ይህን ለማረም የአፍሪካ ሀገራት በአንድነት መታገል አለብን" ብለዋል።

ባለሙያው አፍሪካ በዓለም አቀፍ መድረክ በተለይም በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የሚገባትን ቦታ ለማግኘት ጫና ማድረግ እንዳለባትም አብራርተዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0