አፍሪካ በግብርናው ዘርፍ ዲጂታል ቴክኖሎጂን በስፋት መጠቀም እንዳለባት ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአፍሪካ በግብርናው ዘርፍ ዲጂታል ቴክኖሎጂን በስፋት መጠቀም እንዳለባት ተገለፀ
አፍሪካ በግብርናው ዘርፍ ዲጂታል ቴክኖሎጂን በስፋት መጠቀም እንዳለባት ተገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.12.2025
ሰብስክራይብ

አፍሪካ በግብርናው ዘርፍ ዲጂታል ቴክኖሎጂን በስፋት መጠቀም እንዳለባት ተገለፀ

የአፍሪካ ኅብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ ሰማያዊ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞስስ ቪልካቲ፤ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ትግበራ አኅጉሪቱ በ2030፤ 45 በመቶ የሚሆነውን ምግቧን እንድታመርት ይረዳታል ሲሉ ዛሬ በአዲስ አበባ በተካሄደው የመጀመሪያው የዲጂታል ግብርና ኮንፍረንስ ላይ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ኢፋ ሙለታ በበኩላቸው “ለአህጉሪቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ዘመናዊ የግብርና ሥርዓቶች፣ ሳተላይት ላይ የተመሠረቱ የሰብል ትንተናዎች እና አነስተኛ ገበሬዎችን የሚያበቁ የሞባይል ሥርዓት የዲጂታል መፍትሄዎች አስፈላጊ ናቸው" ሲሉ አፅዕኖት ሰጥተዋል።

ስብሰባው የመረጃ ጥበቃ፣ የዲጂታል ስርዓቶች ተናባቢነት እና ለፈጠራ፣ ማስፋፊያ እንዲሁም ለግሉ ዘርፍ ተሳትፎ አስቻይ የፖሊሲ ምህዳር መፍጠር ላይ ትኩረቱን አድርጎ እስከ ህዳር 24 ድረስ ይካሄዳል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
አፍሪካ በግብርናው ዘርፍ ዲጂታል ቴክኖሎጂን በስፋት መጠቀም እንዳለባት ተገለፀ - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
አፍሪካ በግብርናው ዘርፍ ዲጂታል ቴክኖሎጂን በስፋት መጠቀም እንዳለባት ተገለፀ - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0