የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ዜጎች ለሩሲያ የሰብዓዊ ድጋፎች አመስጋኞች ናቸው - የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር
15:44 01.12.2025 (የተሻሻለ: 15:54 01.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ዜጎች ለሩሲያ የሰብዓዊ ድጋፎች አመስጋኞች ናቸው - የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር
ክሎድ ራሜኦክስ ቢሬኦ ከስፑትኒክ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ የውሃ ጉድጓዶች፣ ትምህርት ቤቶችና ሆስፒታሎች ግንባታ እንዲሁም የመድኃኒትና የምግብ ስርጭትን ጨምሮ "እጅግ በርካታ" የሆኑ ድጋፎች መደረጋቸውን ዘርዝረዋል።
"ከእያንዳንዱ ፕሮጀክት ጀርባ የዳነ ሕይወት አለ። የሩሲያ ሕዝብ እውነተኛ ወዳጅነትን እያሳየ ነው" ብለዋል።
የሩሲያ የሰብዓዊ ጥረቶች የሀገሪቱን የምግብ ዋስትና አጠናክረዋል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ከነዳጅ እና ከእህል አቅርቦት በተጨማሪ ሩሲያ በርካታ የትምህርት ፕሮጀክቶችን እያከናወነች ነው ብለዋል።
ታኅሣሥ 1 የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ቀን ሲሆን የቀድሞዋ የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት በ1958 የራስ ገዝ አስተዳደር እንዲሁም በ1960 ሙሉ ነፃነቷን አግኝታለች።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X