በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች በካይ ጋዝ መቆጣጠሪያ መሣሪያ እንዲገጥሙ በማድረግ የልቀት መጠን ቁጥጥር ሊጀመር ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች በካይ ጋዝ መቆጣጠሪያ መሣሪያ እንዲገጥሙ በማድረግ የልቀት መጠን ቁጥጥር ሊጀመር ነው
በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች በካይ ጋዝ መቆጣጠሪያ መሣሪያ እንዲገጥሙ በማድረግ የልቀት መጠን ቁጥጥር ሊጀመር ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.12.2025
ሰብስክራይብ

በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች በካይ ጋዝ መቆጣጠሪያ መሣሪያ እንዲገጥሙ በማድረግ የልቀት መጠን ቁጥጥር ሊጀመር ነው

ተሽከርካሪዎቹ የሚለቁትን የበካይ ጋዝ መጠን የሚወስን የሕግ መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ ሊገባ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ አስታውቀዋል፡፡

“ይህ ሕግ በሥራ ላይ መዋሉ በካይ ጋዝ እንዲቀንስ ያደርጋል፤ ስለዚህ በቅርቡ ሥራ እንጀምራለን፡፡... ለአሽከርካሪዎች እንዲዘጋጁ የተሰጠው የእፎይታ ግዜ የተጠናቀቀ በመሆኑ፤ በሕግ ሥልጣን የተሰጠው አካል የሚቆጣጠርበት መሣሪያዎች አሉት፡፡ በዚያ መሠረት እየመዘነ በፌደራልም ሆነ በክልል የሚገኙ ተሽከርካሪዎች ተግባራዊ ማድረጋቸውን ያረጋግጣል” ብለዋል፡፡

ቁጥጥሩ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ እንዳይኖሩ ያደረጋል ማለት እንዳልሆነ ያነሱት ሚኒስትሩ፤ መስፈርቱን የማያሟሉ ተሽከርካሪዎች ግን እንደሚታገዱ አስገንዝበዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0