#viral | የቱርክ ባይራክታር ድሮን በሙከራ ወቅት ሰው ተሸካሚ አውሮፕላን በመምታት ታሪክ ሠራ - ኩባንያው
18:47 30.11.2025 (የተሻሻለ: 19:04 30.11.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
#viral | የቱርክ ባይራክታር ድሮን በሙከራ ወቅት ሰው ተሸካሚ አውሮፕላን በመምታት ታሪክ ሠራ - ኩባንያው
አምራቹ ባይካር በሲኖፕ በተደረገ የሙከራ በረራ የውጊያ ድሮኑ ከፍተኛ ፍጥነት ያለውን ጀት በራዳር በመለየት “ፍጹም ትክክል” በሆነ ጥቃት ከእይታ ክልል ውጪ ከአየር ወደ አየር ሚሳኤል በመጠቀም አውድሞታል ሲል አስታውቋል።
ኩባንያው አክሎም እስካሁን ሌላ ምንም ዓይነት ሰው አልባ መሣሪያ የአየር ኢላማን በተሳካ ሁኔታ መትቶ እንደማያውቅ በመግለፅ፤ ባይራክታር የአየር ላይ የውጊያ አቅሙን በማሳየት “በአቪዬሽን ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል” ብሏል።
በአምስት ኤፍ-16 ተዋጊ ጄቶች እና በአኪንጂ ድሮን ክትትል የተካሄደው ሙከራ፤ ሰው አልባ አውሮፕላኑ ከፍተኛ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የጠላት አውሮፕላኖችን ከሩቅ ርቀት የመለየት አቅሙን ያሳየበት ነው ሲል ባይካር አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X