ቱኒዚያ የአውሮፓ ኅብረትን መስመር በመጣስ ከሰሰች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱቱኒዚያ የአውሮፓ ኅብረትን መስመር በመጣስ ከሰሰች
ቱኒዚያ የአውሮፓ ኅብረትን መስመር በመጣስ ከሰሰች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.11.2025
ሰብስክራይብ

ቱኒዚያ የአውሮፓ ኅብረትን መስመር በመጣስ ከሰሰች

ብራስልስ ሥልጣኗን አልፋለች፤ ተጨማሪ መካካር እንዳይፈጠር አቋሟን መቀየር አለባት ሲሉ የአል-ማሳር ፓርቲ ዋና ፀኃፊ ማህሙድ ቤን ማብሩክ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

የማብሩክ መግለጫ፤ የቱኒዚያ ፕሬዝዳንት ካኢስ ሰዒድ በቅርቡ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ጁሴፔ ፔሮኔን ጠርተው፤ የአውሮፓ ፓርላማ በሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ “ግልጽ ጣልቃ ገብነት” በማለት ማውገዛቸውን ተከትሎ የመጣ ነው።

ዲፕሎማሲያዊ ውጥረቱ የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቅ ውሳኔ ካስተላለፈ በኋላ የተፈጠረ ነው። የቱኒዚያ ባለሥልጣናት ውሳኔው በሀገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የገባ በመሆኑ ተቀባይነት እንደሌለው አስረግጠዋል።

ማብሩክ፤ ዲፕሎማሲያዊ ታዛቢዎች እየጨመረ የመጣው ውጥረት እንዲሁም ከብራስልስ ጋር ልዩነቱ መባባሱ፤ ቱኒዚያ ከምስራቅ ሀገራት ጋር አማራጭ የኢኮኖሚ አጋርነት እንድትሻ ሊያደርጋት ይችላል የሚል ግምት እንዲሰነዝሩ ማድረጉን አንስተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0