ጥራትን ባሕል ማድረግ ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላሴ በ12ኛው ብሔራዊ የጥራት ሽልማት ላይ ተናገሩ
12:32 30.11.2025 (የተሻሻለ: 12:44 30.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ጥራትን ባሕል ማድረግ ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላሴ በ12ኛው ብሔራዊ የጥራት ሽልማት ላይ ተናገሩ
የጥራት ሽልማት አሸናፊ መሆን ለተቋማት የልህቀት ጉዞ መጀመሪያ እንጂ መዳረሻ አለመሆኑን ፕሬዝዳንቱ በቤተ-መንግሥት በተካሄደው ሥነ-ሥርዓት ላይ ተናግረዋል።
አክለውም ተቋማት ጥራትን በቋሚነት ማስጠበቅ፣ የሰው ኃይል ብቃትና እውቀትን ማሳደግ እንዲሁም የአመራርና ሠራተኛን ትጋት መጨመር እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል ሲል የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።
በላቀ የአገልግሎት ጥራት አንደኛ ደረጃ በማግኘት ከፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ እጅ ሽልማት የተረከቡ ደርጅቶች፦
ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ፒኤልሲ፣
ሆራይዘን አዲስ ጎማ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣
የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣
ሄኒከን ቢራ ፋብሪካ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X