የአሜሪካ የብዝሃ ዋልታ ዓለም ፍራቻ ደቡብ አፍሪካ ከቡድን 20 እንድትታገድ ምክንያት ነው - ምሁር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአሜሪካ የብዝሃ ዋልታ ዓለም ፍራቻ ደቡብ አፍሪካ ከቡድን 20 እንድትታገድ ምክንያት ነው - ምሁር
የአሜሪካ የብዝሃ ዋልታ ዓለም ፍራቻ ደቡብ አፍሪካ ከቡድን 20 እንድትታገድ ምክንያት ነው - ምሁር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.11.2025
ሰብስክራይብ

የአሜሪካ የብዝሃ ዋልታ ዓለም ፍራቻ ደቡብ አፍሪካ ከቡድን 20 እንድትታገድ ምክንያት ነው - ምሁር

በኬፕ ታውን ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዝዌሌቱ ጆሎቤ፤ አሜሪካ የደቡብ አፍሪካን የቡድን 20 ተሳትፎ የምትቃወመው በዋነኝነት ለፍልስጤም ባላት ግልጽ ድጋፍ በተለይም በቅርቡ በእስራኤል ላይ ከወሰደችው ሕጋዊ እርምጃ ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል፡፡

“የአሜሪካና እና እስራኤል ግንኙነት እና የእስራኤል ድጋፍ ቡድን በአሜሪካ ውስጣዊ ፖለቲካ ላይ ያለው ተፅዕኖ፤ የዩናይትድ ስቴትስን የደቡብ አፍሪካ አቋም ቀርጾታል” ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

ጆሎቤ የሁኔታውን አመልካቾች ሲያብራሩ፤ “አሜሪካ...የብዝሃ ዋልታ ዓለም የሚለውን ሐሳብ እንደ ስጋት ታያለች”፤ በዚህም ምክንያት በዓለም አቀፍ አስተዳደር የደቡብ አፍሪካን ተጽዕኖ ለመገደብ ጥረቶችን እያደረገች ነው ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋል፡፡ ይህም ብቅ እያሉ ባሉ ዓለም አቀፍ ኃይሎች እና የበላይ ሆነው በቆዩት ምዕራባውያን መካከል ያለውን ትልቅ ትግል እንደሚያሳይ ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም አሜሪካ በቡድን 20 ደቡብ አፍሪካ ላይ የምታደርገው ግፊት “ቀደም ሲል ዳር ላይ የነበሩ በርካታ ሀገራት በፍጥነት በሚለዋወጠው ብዝሃ-ዓለም ውስጥ 'ድምፃቸው እየጨመረ መምጣቱን" ሊያመለክት እንደሚችል አስረድተዋል፡፡

ምንም ይሁን ምን “በዓለም አቀፍ ተቋም ውስጥ ያለ አንድ ሀገር በዘፈቀደ ሌላውን ሊያገል አይችልም” ሲሉ ጆሎቤ ሞግተዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0