የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት የሩዋንዳ ኃይሎች አማፂ የሽብር ቡድኖችን በመዋጋት ያከናወኑትን 'አስደናቂ ሥራ' አሞገሱ
19:50 29.11.2025 (የተሻሻለ: 19:54 29.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት የሩዋንዳ ኃይሎች አማፂ የሽብር ቡድኖችን በመዋጋት ያከናወኑትን 'አስደናቂ ሥራ' አሞገሱ
ዳንኤል ቻፖ በግጭት በታወከው በሞዛምቢክ የካቦ ዴልጋዶ ግዛት አንቿቤ ወረዳ የሩዋንዳ የፀጥታ ኃይሎች የስምሪት ስፍራን እንደጎበኙ የሩዋንዳ ወታደራዊ ኃይል አስታውቋል።
"እዚህ ካሉ ወንድሞቻችሁ ጋር አብራችሁ መሥራታችሁን ቀጥሉ፤ ምክንያቱም ያለ ሰላምና ደኅንነት ምንም ዓይነት ልማት ሊመጣ አይችልም" ሲሉ ቻፖ ተናግረዋል።
ጉብኝቱ በአክራሪ ቡድኖች ላይ የሚደረገው የፀረ-ሽምቅ ዘመቻ እየተካሄደ ባለበት ወቅት የመጣ ነው። ወታደራዊ ድሎች ቢመዘገቡም ተለዋዋጭ የሆነው የፀጥታ ሁኔታ ሰብዓዊ ፍላጎቶችን እና የአሸባሪዎች ምልመላ ስጋቶችን አባብሷል።
በኅዳር ወር በተፈፀሙ አዲስ ጥቃቶች ምክንያት በሰሜናዊ ናምፑላ ግዛት ወደ 128 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ቄያቸውን ለቀው እንደተሰደዱ የቅርብ ጊዜ የተመድ መረጃ ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

