የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር የሕግ ዘርፍ ትብብሮችን አፀደቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሚኒስትሮች ምክር ቤት ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር የሕግ ዘርፍ ትብብሮችን አፀደቀ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር የሕግ ዘርፍ ትብብሮችን አፀደቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.11.2025
ሰብስክራይብ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር የሕግ ዘርፍ ትብብሮችን አፀደቀ

በዛሬው ዕለት ባካሄደው 50ኛ መደበኛ ስብሰባ ከቻይና መንግሥት ጋር በደረሰው የወንጀል ጉዳዮች የጋራ የሕግ ትብብር ስምምነት ላይ ተወያይቶ አጽድቋል፡፡

በተጨማሪም ከቻይና እና ብራዚል መንግሥት ጋር የፍርደኞች ማስተላለፍ ስምምነትን በተመሳሳይ አጽድቋል፡፡

አስፈጻሚው አካል ከደቡብ አፍሪካ መንግሥት ጋር የተደረሰውን የአሳልፎ መስጠት ስምምነት እንዲሁ ተቀብሏል፡፡

ምክር ቤቱ ስምምነቶች ቢፀድቁ ኢትዮጵያ ከሀገራቱ ጋር ዉጤታማ የወንጀል መከላከል የሁለትዮሽ ትብብር የሕግ ማዕቀፍ ለመፍጠር ያስችላታል በማለት ረቂቅ አዋጆቹን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0