የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ሩዋንዳ መሪዎች በሚቀጥለው ሳምንት ትራምፕ ያሸማገሉትን የሰላም ስምምነት በዋሽንግተን ዲሲ እንደሚፈራረሙ ተገለጸ
15:08 29.11.2025 (የተሻሻለ: 15:14 29.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ሩዋንዳ መሪዎች በሚቀጥለው ሳምንት ትራምፕ ያሸማገሉትን የሰላም ስምምነት በዋሽንግተን ዲሲ እንደሚፈራረሙ ተገለጸ
ለህዳር 25 የታቀደው ይህ ስብሰባ፤ አሜሪካ በጦርነት በምትታመሰው ምስራቅ ኮንጎ ያለውን ውጥረት ለመፍታት እንዲሁም በማዕድን በበለጸገው ክልል የምዕራባውያን የማዕድን ኢንቨስትመንቶችን ለመዘርጋት የምታደርገው ጥረት አካል ነው ሲል የምዕራባውያን ሚዲያ ዘገባ አመልክቷል።
የኮንጎ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ሺሰኬዲ ቃልአቀባይ የታቀደውን የስምምነት ፊርማ አረጋግጠዋል ተብሏል። የትራምፕ አስተዳደር በሰኔ ወር ያደራደረው ስምምነት ላይ የተመሠረተ ይሆናል።
የዲፕሎማሲ ጥረቱ የመጣው በሩዋንዳ ይደገፋል የሚባለው የኤም23 አማፂ ቡድን በዚህ ዓመት በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞት እና በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩት ደግሞ መፈናቀል ምክንያት የሆነውን ውጊያ ዳግም መቀጠሉን ተከትሎ ነው። ኪጋሊ በግጭቱ ውስጥ ምንም አይነት ተሳትፎ የለኝም ስትል ማስተባበሏን ቀጥላለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X