ኢትዮጵያ በ2050 የአቪዬሽን የጋዝ ልቀትን ዜሮ ለማድረስ ማቀዷን ገለፀች
12:34 29.11.2025 (የተሻሻለ: 12:44 29.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በ2050 የአቪዬሽን የጋዝ ልቀትን ዜሮ ለማድረስ ማቀዷን ገለፀች
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ ሀገሪቱ የትራንስፖርት ዘርፉን ዘመናዊ ከማድረግ ባሻገር የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀትንና የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ ጥረት እያደረገች እንደሆነ በዘላቂ የአቪዬሽን ነዳጅ የአዋጭነት ጥናት ውጤት ዙሪያ በተዘጋጀ መድረክ ላይ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቀልበስ ግንባር ቀደም ሚና እየተወጣች እንደምትገኝም በመድረኩ ተመላክቷል፡፡
ሀገሪቱ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በአካባቢ ጥበቃ እንዲሁም በአረንጓዴ አሻራ ተነሳሽነት ያከናወነቻቸው ተግባራቶች በአብነት ተነስተዋል፡፡
ዘላቂ አቪዬሽን ነዳጅ ከአቪዬሽን ኢንዱስትሪ 80 በመቶ የካርበን ልቀትን ለመቀነስ የሚያስችል የኃይል አማራጭ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X