የመንግሥት ሠራተኞች ከ2019 ጀምሮ የጤና መድን ተጠቃሚ ይሆናሉ ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየመንግሥት ሠራተኞች ከ2019 ጀምሮ የጤና መድን ተጠቃሚ ይሆናሉ ተባለ
የመንግሥት ሠራተኞች ከ2019 ጀምሮ የጤና መድን ተጠቃሚ ይሆናሉ ተባለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.11.2025
ሰብስክራይብ

የመንግሥት ሠራተኞች ከ2019 ጀምሮ የጤና መድን ተጠቃሚ ይሆናሉ ተባለ

አገልግሎቱ በመጪው ዓመት ለማስጀመር በገንዘብ ሚኒስቴር 4.5 ቢሊዮን ብር መጽደቁን የኢትዮጵያ ጤና መድን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ተስፋዬ ወርቁ አስታውቀዋል፡፡

‍በዘንድሮው ዓመት በጤናው ዘርፍ የተሰማሩ ከ500 ሺህ በላይ ሠራተኞች ለአገልግሎቱ መመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡

“መደበኛ በሆኑ የሥራ መስኮች የተሰማሩ ዜጎች የጤና መድን አገልግሎት እንዲያገኙ ታስቦ የተዘጋጀው የማኅበራዊ ጤና መድን አገልግሎት በአዋጅና ደንብ ከጸደቀ 14 ዓመታትን ቢያስቆጥርም ሳይተገበር ቆይቷል፤ ዘንድሮ ግን የተሻለ ተስፋ አለ” ሲሉ ገልፀዋል፡፡

አዋጁ ከሠራተኛው ደመወዝ ሦስት በመቶው እንዲቆረጥና የፌዴራልና የክልል መንግሥታትም ለተቀጣሪዎቻቸው ይህን እንዲሸፍኑ ይደነግጋል።

ዋና ዳይሬክተር በቀጣዩ ዓመት ሁሉም የመንግሥት ሠራተኛ የጤና መድን ተጠቃሚ እንዲሆን የፌዴራልም ሆነ የክልል መንግሥታት በጀት ይይዛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ መናገራቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0