ኢትዮጵያ ከሩስያ ጋር የጀመረቻቸው የቴክኖሎጂ ዘርፍ ትብብሮች ለእውቀት ሽግግር በር ከፋች ናቸው - ባለሙያ
19:29 28.11.2025 (የተሻሻለ: 19:34 28.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከሩስያ ጋር የጀመረቻቸው የቴክኖሎጂ ዘርፍ ትብብሮች ለእውቀት ሽግግር በር ከፋች ናቸው - ባለሙያ
ከዘርፉ ተለዋዋጭነት አንፃር ዘመኑ ከደረሰበት የቴክኖሎጂ አቅም ላይ ለመድረስ ልምድ ካላት ሞስኮ ጋር መጣመሩ ጠንካራ አቅም ይፈጥራል ሲሉ የሶፍትዌር ፕሮግራም፣ ሳይበር ደህንነት፣ ኤአይ ዲቨሎፐር የሆኑት አቤል በነበሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
ሁለቱ አገራት የብሪክስ አጋር እንደመሆናቸው የፖለቲካዊ ትብብሩ ወደ ቴክኖሎጂ በመለወጥ ተጨባጭ ውጤት እንደሚያስገኝ አንስተዋል፡፡
“እውቅት ካጋሩን፣ ብቁ ባለሙያዎችን መፍጠር ከተቻለ ሞዴሎች ማብቃት የማይደረግበት ምክንያት የለም፡፡ የእኛ ቋንቋ፣ የእኛ የሆነ ነገር፣ ከእኛ ባህል ጋር እኛን የሚመስል ቴክኖሊጂ መፍጠር ያስችለናል ማለት ነው።
አቤል በነበሩ፣ ከአቅም ግንባታ እና የዕውቀት ሽግግር ባለፈ አስቻይ የሆነ የመሠረተ ልማት መገንባ እንዲቻል እገዛ እንደሚኖራቸው ባለሙያው ጠቅሰዋል፡፡
“በሳተላይት አንፃር ስናየው ሩሲያ አንጋፋ፤ በጣም በርካታ ሳተላይቶች እና የላቀ ልምድ ያላት አገራት ናት። እና ያ ልምድ ወደ እኛ ሲመጣ የጂኦ ስፓሻል ዳታ ሀብቶቻችንን የማወቅ አቅማችንን በማሳደግ በተለይ በግብርና፣ በአየር ንብረት፣ በማዕድን ጉዳዮች ላይ በደንብ ልንጠቀምበት እንችላለን፤“ ሲሉ አስረድተዋል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X