ኢትዮጵያ በ2025 የዓለም አቀፍ የሥራ ፈጠራ ሳምንት በዓለም ቀዳሚውን ደረጃ ይዛ አጠናቀቀች
18:33 28.11.2025 (የተሻሻለ: 18:34 28.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በ2025 የዓለም አቀፍ የሥራ ፈጠራ ሳምንት በዓለም ቀዳሚውን ደረጃ ይዛ አጠናቀቀች
እውቅናው "አብረን እንገንባ" በሚል መሪ ቃል በተከበረው የ2025 የዓለም አቀፍ የሥራ ፈጠራ ሳምንት ላይ ተበርክቷል፡፡
ሀገሪቱ በዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የተባለውን 11,042 ሁነቶች በሥራ ፈጠራ ዘርፍ ማስተናገዷ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
“ይህ ስኬት ባለፈው ዓመት በዓለም 8ኛ እና ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃ ሆኖ በተመዘገበው ውጤት ላይ ከፍተኛ መሻሻል ያሳያል፤ ይህም የሀገሪቱ ቁርጠኝነትና የትብብር ጥረቶች ውጤት ነው” ሲሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል ገልጸዋል።
ሚኒስትሯ አክለውም ዜጎች ሥራ ፈጠራን እንደ ግለሰብም ሆነ እንደ ሀገር ኃላፊነት እንዲቀበሉ አሳስበዋል።
በአገሪቱ የሥራ ፈጠራ ዘርፍ፦
ከ700,000 በላይ ዜጎች ተሳትፈዋል
በ13 ክልሎች ያሉ ከ600 በላይ ከተሞችን ያካትታል
ከ300 በላይ አጋር ተቋማት ተሳትፎን አድርገዋል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
/