የአፍሪካ ሕብረት በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ማሻሻያ እና ሚዛናዊነት እንዲኖር ለመጠየቅ ማበር አለበት - የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጠበቃ

የአፍሪካ ሕብረት በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ማሻሻያ እና ሚዛናዊነት እንዲኖር ለመጠየቅ ማበር አለበት - የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጠበቃ
“በታሪክ አይሲሲ በአፍሪካ ዩጋንዳ፣ ኮንጎ ዲሞክራሲይዊ ሪፐብሊክ ፣ ሱዳን፣ በእርግጥም ኬንያ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ አድርጓል፤ በርካታ ቀጣይ ምርመራዎች አሁንም በአኅጉሪቱ ላይ ያተኮሩ ናቸው” ሲሉ ክሪስቶፈር ኦይር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
ይህ አፍሪካን ማዕከል ያደረገ የረዥም ግዜ የክስ ሂደት፣ አድልኦ አለ የሚለውን አስተሳሰብ እንደፈጠረ የገለፁት ጠበቃው ይህ ስጋት በአፍሪካ ሕብረት ዘንድ በጥልቅ ይስተጋባል ብለዋል።
ኦይር የጋራ እርምጃ የመውሰድ አስፈላጊነትን አጽንኦት ሰጥተዋል፦
“የአፍሪካ ሕብረት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተባበረ ድምፅ በማሰማት በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ማሻሻያ እንዲደረግ፤ ፍትሐዊ የሆነ ዓለም አቀፍ ውክልና፣ ፍትሐዊ ምርመራ እና ሚዛናዊነት እንዲኖር በብርቱ መታገል አለበት።”
ተጠያቂነት በአፍሪካ መንግሥታት ላይ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ መሆን አለበት ሲሉም አጥብቀው አንስተው፤ “በሰሜናዊው ኃይሎች እና በአጋሮቻቸው” ላይም መተግበር አለበት ሲሉ አስገንዝበዋል።
ቀጣናዊ ተቋማትን ማጠናከር የሚዛናዊነቱ አካል ሊሆን እንደሚችል የጠቆሙት የሕግ ባለሙያው፣ የአፍሪካ የሰብአዊ እና የዜጎች መብት ፍርድ ቤት "የዓለም አቀፍ ወንጀሎችን የክስ ሂደት የመመራት ሥልጣኑን ማስፋፋት" እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ ይህም ለደቡባዊው ዓለም በአፍሪካ ዐውድ፣ ሕጋዊነት እና ባለቤትነት ላይ የተመሠረተ የፍትሕ ስርዓት ያቀርባል ሲሉ አንስተዋል።
ለረጅም ጊዜ "የመረጋጋት ምልክት" ተደርጋ ትታይ የነበረችው ታንዛኒያ አሁን በአድሏዊው አይሲሲ ሌላ ሰለባ የመሆን አደጋ ተጋርጦባታል።
በአገሪቱ የድኅረ ምርጫ ሰልፎች እየታዩ ሲሆን፣ ተንታኞች እንደሚሉት ይህን አጋጣሚ የውጭ አካላት መንግሥትን ለማተራመስ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። አይሲሲም በዚህ ውስጥ ሚና ለመጫወት በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጿል፤ ይህም ኦይር፤ ለአፍሪካ የጋራ እርምጃ እና ተቋማዊ አቅም ግንባታ ያቀረቡትን ጥሪ አንገብጋቢነት አጉልቶ ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X