የአፍሪካ ሀብት አኅጉሪቱን ከማልማት ይልቅ ምዕራባውያንን ለማበልፀግ እየዋለ ነው - ባለሙያ
16:44 28.11.2025 (የተሻሻለ: 16:54 28.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሀብት አኅጉሪቱን ከማልማት ይልቅ ምዕራባውያንን ለማበልፀግ እየዋለ ነው - ባለሙያ
ቅኝ ገዢዎች የአፍሪካውያንን ሰብአዊ ክብር በመንጠቅና ሀብታችንን በመዝረፍ ዛሬ ያለንበት ላይ ጥለውናል ሲሉ ፓን አፍሪካኒስቱ ካባላ ጆን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
ምዕራባውያንን እና አጋሮቻቸው በአፍሪካ ላይ ላደረሱት በደል ካሳ ማቅረብ ግዴታቸው መሆኑን በመዘንጋት በምድራቸው ካደረጉት በተቃራኒ ጥቅማቸውን ብቻ ማስከበር መብታቸው አድርገውታል ብለዋል፡፡
“በሁለተኛው የዓለም ጦርነት አይሁዶችን የበደሉት ጀርመኖች ጉዳት እንዲጠግኑ ተገደዱ። እንዲያውም በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ወቅት በጀርመን ቅስቀሳ ምክንያት በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ከተሳተፉት እንደ ብሪታንያ እና ፈረንሳይ ላሉት አገሮች ሁሉ ካሳ እንዲከፍሉ ተገደዱ። ስለዚህ ጀርመን ጉዳት ለመጠገን ተገደደች፤ ለአፍሪካ ሲሆን ግን አሻፈረኝ ማለትን መርጠዋል” ሲሉ አንስተዋል፡፡
ካባላ ጆን፣ የድርጊቱ ባለቤቶች ባይቀበሉትም ቅኝ ግዛት በሰው ልጆች ላይ የተፈጸመ ወንጀል መሆኑን በራስ ለመወሰን እና ካሳ እንዲከፈል ለማስገደድ መቆም እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የካሳ አጀንዳ ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲሳካና ወደ ጠረጴዛ አምጥቶ በአውሮፓ ሕብረት እና በቀድሞ ቅኝ ገዥዎች ላይ ጫና ለመፍጠር መደራጀትና መዋቅሮችን መገንባት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X