እስራኤል በሶሪያዋን ቤይት ጂን ከተማ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ንፁሃን ላይ ሞትና ጉዳት ማስከተሉ ተዘገበ

ሰብስክራይብ

እስራኤል በሶሪያዋን ቤይት ጂን ከተማ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ንፁሃን ላይ ሞትና ጉዳት ማስከተሉ ተዘገበ

እስራኤል በደማስቆ ግዛት ውስጥ በምትገኘው ቤይት ጂን ከተማ ላይ በፈፀመችው ጥቃት ሴቶችን እና ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 10 ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን እና ተጨማሪ ተጎጂዎችም ፍርስራሽ ስር ተቀብረው ሊሆን እንደሚችል የሶሪያ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

በቦምብ የታገዘው ከፍተኛ የጥቃት እርምጃው ነዋሪዎች ተጨማሪ አደጋ እንዳይደርስ በመስጋት ወደ ጎረቤት ከተሞች በጅምላ እንዲሰደዱ አድርጓል። ምንም እንኳን እስካሁን ያልተረጋገጠ ቢሆንም ጥቃቱ የተጀመረው የእስራኤል ወታደሮች በአካባቢው ወረራ ሲያካሂዱ በአካባቢው ነዋሪዎች ከተከበቡ በኋላ ነው ሲሉ የሶሪያ ምንጮች ገልፀዋል።

ከሶሪያ ዋና ከተማ 50 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ በምትገኘው ቤይት ጂን የንጹሐን ዜጎች ሞት ቢጨምርም የእስራኤል ኦፕሬሽን መቀጠሉ ተገልጿል።

ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ ተንቀሳቃሽ ምስል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0